በአዳማ ከተማ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች ተከናውነዋል-ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ካለፈው አንድ አመት ወዲህ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች መከናወናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ከዚህ ቀደም በመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት ያቋረጡትን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማከናወናቸውን እና የንግድ ሱቅ ከፍተው መስራት መቻላቸውንም ነዋሪዎቹ አንስተዋል።

የአዳማ ከተማ በየዓመቱ ስሟ በሚነሳበት የጎርፍ አደጋ በ2009 ዓ.ም ክረምት ጉዳት አለማድረሱን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

ሆኖም ያልተፈቱ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን ነዋሪዎቹ ይጠቅሳሉ፤ በከተማዋ መሀል አካባቢ ኤሌክትሪክ የማያገኙ መንደሮች፣ የሃይል መቆራረጥና በአቧራ የተሸፈኑና የማይመቹ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መኖራቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ ባለፈም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችና የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትወርክ መቆራረጥም ነዋሪዎቹ አሁንም ያልተፈታላቸው ችግር መሆኑን ነው የገለፁት።

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ በከተማዋ ተዘዋውራ ባደረገችው ቅኝት በርካታ የከተማዋ ወጣቶች ካለፈው ዓመት ወዲህ በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ነግረዋታል።

አሁን ላይ ከ250 ሺህ ብር ጀምሮ የመስሪያ ብድር ገንዘብና ከ300 ካሬ ሜትር ያላነሰ ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ በማግኘት ወደ ስራ ተሰማርተናል ነው ያሉት።

የተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በአፋጣኝ ወደ ስራ ማስገባት ላይና ለወጣቶች ስራ መፍጠሪያ የሚሰጡ ቦታዎች ላይ የሚታዩ የመሰረተ ልማት ችግሮችም ፈታኝ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥ በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማው የአገልግሎት አሰጣጡ ያለደላላ የማይፈጸም መሆኑ በመለየቱ፥ የደላላውን መረብ ለመበጣጠስ የሚያስችሉ የአደረጃጀት ማሻሻያዎች ተደርገዋል።

ለህዝብ ቅሬታ መንስኤ የሆኑ የተጓተቱ የመሰረተ ልማት ስራዎችን የማስጨረስ ስራዎች መከናወናቸውንም ነው ያነሱት።

በተለያዩ የስራ መስኮች በተደረገ ልየታም ባለፈው ዓመት ብቻ 15 ሺህ የሚሆኑ ስራ ፈላጊ ህብረተሰቦች ወደ ስራ እንዲሰማሩ መደረጉን ጠቁመዋል።

በመንግስት የተመዘገቡ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችም በህገ ወጥ መልኩ በግለሰቦች እጅ በመገኘታቸው፥ በርካታ ቤቶችን በመቀማት ለስራ ፈላጊ ዜጎችና መኖሪያ ቤት ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተላለፍ ተችሏል።

በህጋዊና በህገወጥ መልኩ ተይዘው እስከ 25 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ያልለሙ የኢንቨስትመንት መሬቶችን፥ ለተሻሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችና ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ወደ መሬት ባንክ የማስመለስ ስራ ተከናውኗል።

ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግም ከተማዋን ከጎርፍ መከላከል የሚያስችል ስራ ተሰርቷል ነው የተባለው።

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በህዝብ ተሳትፎ መቅረፍ፣ ያልተመለሱ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ፣ ከተማዋን ጽዱና አረንጓዴ ማድረግ፣ የሰነድ አልባ ቤቶችን ጉዳይ ማጠናቀቅ፣ የመሬት ካዳስተር ስራን ማከናወንና የከተማዋን አዲስ መሪ ፕላን ማጠናቀቅ፥ የከተማ አስተዳደሩ የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንም ከንቲባዋ አስረድተዋል።
በአዳማ ከተማ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች ተከናውነዋል-ነዋሪዎች አዲስ አበባ ፣ ህዳር 26 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ካለፈው አንድ አመት ወዲህ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች መከናወናቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ። ከዚህ ቀደም በመሰረተ ልማት አለመሟላት ምክንያት ያቋረጡትን የመኖሪያ ቤት ግንባታ ማከናወናቸውን እና የንግድ ሱቅ ከፍተው መስራት መቻላቸውንም ነዋሪዎቹ አንስተዋል። የአዳማ ከተማ በየዓመቱ ስሟ በሚነሳበት የጎርፍ አደጋ በ2009 ዓ.ም ክረምት ጉዳት አለማድረሱን ነዋሪዎች ጠቁመዋል። ሆኖም ያልተፈቱ በርካታ ችግሮች መኖራቸውን ነዋሪዎቹ ይጠቅሳሉ፤ በከተማዋ መሀል አካባቢ ኤሌክትሪክ የማያገኙ መንደሮች፣ የሃይል መቆራረጥና በአቧራ የተሸፈኑና የማይመቹ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መኖራቸውን አስረድተዋል። ከዚህ ባለፈም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችና የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትወርክ መቆራረጥም ነዋሪዎቹ አሁንም ያልተፈታላቸው ችግር መሆኑን ነው የገለፁት። የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ በከተማዋ ተዘዋውራ ባደረገችው ቅኝት በርካታ የከተማዋ ወጣቶች ካለፈው ዓመት ወዲህ በተፈጠረላቸው የስራ እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ነግረዋታል። አሁን ላይ ከ250 ሺህ ብር ጀምሮ የመስሪያ ብድር ገንዘብና ከ300 ካሬ ሜትር ያላነሰ ቦታ ከከተማ አስተዳደሩ በማግኘት ወደ ስራ ተሰማርተናል ነው ያሉት። የተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን በአፋጣኝ ወደ ስራ ማስገባት ላይና ለወጣቶች ስራ መፍጠሪያ የሚሰጡ ቦታዎች ላይ የሚታዩ የመሰረተ ልማት ችግሮችም ፈታኝ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የአዳማ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፥ በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማው የአገልግሎት አሰጣጡ ያለደላላ የማይፈጸም መሆኑ በመለየቱ፥ የደላላውን መረብ ለመበጣጠስ የሚያስችሉ የአደረጃጀት ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ለህዝብ ቅሬታ መንስኤ የሆኑ የተጓተቱ የመሰረተ ልማት ስራዎችን የማስጨረስ ስራዎች መከናወናቸውንም ነው ያነሱት። በተለያዩ የስራ መስኮች በተደረገ ልየታም ባለፈው ዓመት ብቻ 15 ሺህ የሚሆኑ ስራ ፈላጊ ህብረተሰቦች ወደ ስራ እንዲሰማሩ መደረጉን ጠቁመዋል። በመንግስት የተመዘገቡ የመኖሪያና የንግድ ቤቶችም በህገ ወጥ መልኩ በግለሰቦች እጅ በመገኘታቸው፥ በርካታ ቤቶችን በመቀማት ለስራ ፈላጊ ዜጎችና መኖሪያ ቤት ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተላለፍ ተችሏል። በህጋዊና በህገወጥ መልኩ ተይዘው እስከ 25 ዓመት ለሚደርስ ጊዜ ያልለሙ የኢንቨስትመንት መሬቶችን፥ ለተሻሉ የኢንቨስትመንት ስራዎችና ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ እንዲሁም ወደ መሬት ባንክ የማስመለስ ስራ ተከናውኗል። ከ150 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግም ከተማዋን ከጎርፍ መከላከል የሚያስችል ስራ ተሰርቷል ነው የተባለው። የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በህዝብ ተሳትፎ መቅረፍ፣ ያልተመለሱ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ፣ ከተማዋን ጽዱና አረንጓዴ ማድረግ፣ የሰነድ አልባ ቤቶችን ጉዳይ ማጠናቀቅ፣ የመሬት ካዳስተር ስራን ማከናወንና የከተማዋን አዲስ መሪ ፕላን ማጠናቀቅ፥ የከተማ አስተዳደሩ የዚህ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውንም ከንቲባዋ አስረድተዋል።
0 Comments 0 Shares