በአፍዴራ በቱሪስቶች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በቱሪስቶች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሎ አፍኬኤ እንደገለጹት በወረዳው ህዳር 24 ቀን ምሽት አራት ሰዓት ተኩል ተኩስ በመክፈት በተፈፀመው በዚሁ ጥቃት ህይወቱ ካለፈው ሌላ አንድ ሰው የመቁሰል ጉዳት ደርሶበታል።

ህይወቱ ያለፈው የውጭ ዜጋ ሲሆን፥ የመቁሰል ጉዳቱ የደረሰበት ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው።

ጉዳቱ የደረሰባቸው ሁለቱ ሰዎች አብረው ከነበሩ ሌሎች በርካታ ቱሪስቶች ተነጥለው በመሄድ ፎቶ በማንሳት ላይ እንዳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ እንደሆነ ተመልክቷል።

የአፍዴራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሳ መሃመድ በበኩላቸው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጨለማን ተገን በማድረግ ጥቃቱን መፈፀማቸውን አስታውቀዋል።

በወረዳው ልዩ ስሙ ኤርታአሌ የተባለውን የቱሪስት ስፍራን ለመጎብኘት በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩ ቱሪስቶች ላይ ተኩስ ተከፍቶ በተፈፀመው ጥቃት ጉዳቱ ሊደርስ እንደቻለ አመልክተዋል።

በዚህም በተፈጸበት ጥቃት ሕይወቱ ባለፈው ጀርመናዊ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ በጎብኚው ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል መንግስት ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ ከተጣራ በኋላ ይፋ እንደሚደረግም ተጠቁሟል።

ወንጀሉ በፀረ-ሠላም ኃይሎች መፈፀሙን የገለፀው ፅህፈት ቤቱ፥ በአሁኑ ወቅት አካባቢው ሠላማዊ እና የተረጋጋ መሆኑን ነው ያመለከተው።

የመቁሰል ጉዳት የደረሰበት መቐሌ ወደሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላኩም ታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
በአፍዴራ በቱሪስቶች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት አለፈ አዲስ አበባ፣ ህዳር 26፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋር ክልል አፍዴራ ወረዳ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በቱሪስቶች ላይ በፈጸሙት ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አሎ አፍኬኤ እንደገለጹት በወረዳው ህዳር 24 ቀን ምሽት አራት ሰዓት ተኩል ተኩስ በመክፈት በተፈፀመው በዚሁ ጥቃት ህይወቱ ካለፈው ሌላ አንድ ሰው የመቁሰል ጉዳት ደርሶበታል። ህይወቱ ያለፈው የውጭ ዜጋ ሲሆን፥ የመቁሰል ጉዳቱ የደረሰበት ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። ጉዳቱ የደረሰባቸው ሁለቱ ሰዎች አብረው ከነበሩ ሌሎች በርካታ ቱሪስቶች ተነጥለው በመሄድ ፎቶ በማንሳት ላይ እንዳሉ በተከፈተባቸው ተኩስ እንደሆነ ተመልክቷል። የአፍዴራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሳ መሃመድ በበኩላቸው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ጨለማን ተገን በማድረግ ጥቃቱን መፈፀማቸውን አስታውቀዋል። በወረዳው ልዩ ስሙ ኤርታአሌ የተባለውን የቱሪስት ስፍራን ለመጎብኘት በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩ ቱሪስቶች ላይ ተኩስ ተከፍቶ በተፈፀመው ጥቃት ጉዳቱ ሊደርስ እንደቻለ አመልክተዋል። በዚህም በተፈጸበት ጥቃት ሕይወቱ ባለፈው ጀርመናዊ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገልጿል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ በጎብኚው ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል መንግስት ምርመራ እያደረገ ይገኛል። ድርጊቱ ሙሉ በሙሉ ከተጣራ በኋላ ይፋ እንደሚደረግም ተጠቁሟል። ወንጀሉ በፀረ-ሠላም ኃይሎች መፈፀሙን የገለፀው ፅህፈት ቤቱ፥ በአሁኑ ወቅት አካባቢው ሠላማዊ እና የተረጋጋ መሆኑን ነው ያመለከተው። የመቁሰል ጉዳት የደረሰበት መቐሌ ወደሚገኘው አይደር ሪፈራል ሆስፒታል መላኩም ታውቋል። ምንጭ፦ ኢዜአ
0 Comments 0 Shares