በሳዑዲ አረቢያ በሙስና ምክንያት የታሰሩት ልኡላንና ባለሀብቶች ገንዘብ ከፍለው በይቅርታ ሊወጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳዑዲ አረቢያ በሙስና መንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ልኡላንና ባለህበቶች ከንዘብ ከፍለው በይቅርታ እንዲወጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ።

የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቁት፥ አብዛኞቹ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ልኡላንና ባለህበቶች ገንዘብ ከፍለው በይቅርታ ለመውጣት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ከስምምነት ደርሰዋል።

አዲስ የተቋቋመው የሳዑዲ አረቢያ የፀረ ሙስና አካል ባሳለፍነው ጥቅምት ወር 11 ልኡላንን፣ አራት ሚኒስትሮች እና የቀድሞ ሚኒስትሮችን እንዲሁም በርካታ ባለሀብቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።

የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ 320 ሰዎች ለጥያቄ እንዲቀርቡ የተጠሩ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 159 በአሁኑ ጊዜ በቁጥጥር ስር ይገኛሉ።

ከእነዚ ውስጥ የሙስና ተግባሩን አልፈፀምኩም ብለው የሚከራከሩ እና ለይቅርታ የቀረበውን የገንዘብ ስምምነት የማይቀበሉ ሰዎች ክስ የሚመሰረትባቸው መሆኑም መግለጫው አመልክቷል።

ባሳለፍነው ሳምንት ልኡል ማቲን ቢን አብዱላህ በቀረበው የይቅርታ መደራደሪያ መሰረት ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከፍለው ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በቁጥጥር ስር የዋሉት ልኡላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለሀብቶች በሪያድ የሚገኝ ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ነው ታስረው የሚገኙት።

ግለሰቦቹ በሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሰልማን ትእዛዝ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑም ይታወሳል።

አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሰልማን ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ያዋሉት የሀገሪቱን ስልጣን ለመቆጣጠር ነው በሚል የቀረበባቸውን ወቀሳ አስተባብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
በሳዑዲ አረቢያ በሙስና ምክንያት የታሰሩት ልኡላንና ባለሀብቶች ገንዘብ ከፍለው በይቅርታ ሊወጡ ነው አዲስ አበባ፣ ህዳር 27፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሳዑዲ አረቢያ በሙስና መንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የሚገኙ ልኡላንና ባለህበቶች ከንዘብ ከፍለው በይቅርታ እንዲወጡ ከስምምነት ላይ መደረሱ ተገለፀ። የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ እንዳስታወቁት፥ አብዛኞቹ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ልኡላንና ባለህበቶች ገንዘብ ከፍለው በይቅርታ ለመውጣት ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ከስምምነት ደርሰዋል። አዲስ የተቋቋመው የሳዑዲ አረቢያ የፀረ ሙስና አካል ባሳለፍነው ጥቅምት ወር 11 ልኡላንን፣ አራት ሚኒስትሮች እና የቀድሞ ሚኒስትሮችን እንዲሁም በርካታ ባለሀብቶችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል። የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያወጣው መግለጫ እንደሚያመለክተው፤ 320 ሰዎች ለጥያቄ እንዲቀርቡ የተጠሩ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 159 በአሁኑ ጊዜ በቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ከእነዚ ውስጥ የሙስና ተግባሩን አልፈፀምኩም ብለው የሚከራከሩ እና ለይቅርታ የቀረበውን የገንዘብ ስምምነት የማይቀበሉ ሰዎች ክስ የሚመሰረትባቸው መሆኑም መግለጫው አመልክቷል። ባሳለፍነው ሳምንት ልኡል ማቲን ቢን አብዱላህ በቀረበው የይቅርታ መደራደሪያ መሰረት ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከፍለው ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል። ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በቁጥጥር ስር የዋሉት ልኡላን፣ ሚኒስትሮች እና ባለሀብቶች በሪያድ የሚገኝ ቅንጡ ሆቴል ውስጥ ነው ታስረው የሚገኙት። ግለሰቦቹ በሳዑዲ አረቢያው አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሰልማን ትእዛዝ በቁጥጥር ስር የዋሉ መሆኑም ይታወሳል። አልጋ ወራሽ ልኡል መሀመድ ቢን ሰልማን ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር ያዋሉት የሀገሪቱን ስልጣን ለመቆጣጠር ነው በሚል የቀረበባቸውን ወቀሳ አስተባብለዋል። ምንጭ፦ ቢቢሲ
0 Comments 0 Shares