ዋልያዎቹ በሴካፋ ዋንጫ ከዩጋንዳ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2017 የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዛሬ ጨዋታውን አድርጓል።
ከዩጋንዳ ጋር የተደረገው የምድቡ ሶስተኛ ጨዋታም አንድ አቻ ተጠናቋል።
ኢትዮጵያ ጨዋታውን 1 ለ 0 እየመራች ብትቆይም፥ በጨዋታው መጠናቀቂያ አካባቢ ዩጋንዳዎች አቻ መሆን ችለዋል።
ቡድኑ ባለፈው ሃሙስ በቡሩንዲ አቻው 4 ለ 1 መሸነፉ የሚታወስ ነው።
በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ ደግሞ ደቡብ ሱዳንን 3 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።
ውጤቱን ተከትሎም ዩጋንዳ በ5 ነጥብ ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።
የኢትዮጵያ የማለፍ እድል ደግሞ በነገው ጨዋታ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።
ነገ ደቡብ ሱዳን ቡሩንዲን በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ከቻለች ዋልያዎቹ ግማሽ ፍጻሜውን ይቀላቀላሉ፤ ይህ ካልሆነ ግን ከውድድሩ የሚሰናበቱ ይሆናል።
ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ

0 Comments
0 Shares