ዳይ እየተሰዳደብን ...
«ዘውድአለም ታደሰ»
ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖልኛል። ጭራሽ እየሩሳሌምን ለእስራኤል አሳልፈን አንሰጥም! አንሰጥም! አንሰጥም!እንሰጣለን! እንሰጣለን! እንሰጣለን! ... የሚሉ መፈክሮችን የሚያሰሙ በሁለት ጎራ የተከፈሉ ግሩፖችን እያየሁ ነው!! ኡኡቴ አሉ እማማ ፈለቁ ባላቸው እሩብ ኪሎ ስጋ ይዞ የገቡ እለት :D
ማይ ብራዘር ...... የአለም የመጨረሻ ችጋራም ፣ ደሃ ፣ ብድራም፣ ዱቤያም፣ ረሃብተኛ፣ ኋላቀር፣ ጎስቋላ ሐገር ላይ ተቀምጦ በኢየሩሳሌም ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን መሞከር ቲኒሽ ኪላሽ አያረግም? እስቲ ኢየሩሳሌምን ለፓለስታይን ከማስመለስህ በፊት ወደብህን አስመልስ፣ እስቲ ጅቡቲን...