በስፔን የካታሎኒያ ግዛት ፓርላማ ግዛቲቱ ነፃ አገር መሆኗን ማወጁን ተከትሎ የአገሪቱ ሴኔት ግዛቲቱ ቀጥታ በማድሪድ እንድትተዳደር ወሰነ።
135 መቀመጫ ባለው የካታሎኒያ ፓርላማ 70 አባላት ግዛቲቱ ከስፔን ተገንጥላ ነፃ አገር እንድትሆን የቀረበውን ሞሽን ሲደግፉ፥ 10 ደግሞ ተቃውመዋል።
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራጆይ ከፓርላማው ውሳኔ በኋላ ስፔናውያን እንዳይደናገጡ እና እንዲረጋጉ አሳስበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ሴኔት ፊት ቀርበው የካታሎኒያ ግዛት ቀጥታ በማድሪድ እንድትተዳደር ያቀረቡት ጥያቄ ፀድቋል።
አሁን ያለውን የካታሎኒያ አስተዳደር ቤተሰብን እየከፋፈለ እና ማህበረሰብን እየሰነጣጠቀ ያለ ብለውም ነበር የከሰሱት።
በዚህ ብዙ ሰዎች ተሰቃይተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ራጆይ፥ ሁኔታው በንግድ ሰዎች ዘንድ መተማመንን አጥፍቶ ከግዛቲቱ እንዲወጡ እያደረገ መሆኑን ነው ያመለከቱት።
የስፔን ህገመንግስት በቀውስ ወቅት ግዛቲቱን ቀጥታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እንዲያስተዳደር የሚፈቅድ አንቀፅን ያካተተ ሲሆን፥ ሴኔቱ ይህ አንቀፅ እንዲተገበር ነው የወሰነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔያቸውን ሰብስበው በቀጣይ እርምጃ ላይ ይመክራሉ ተብሏል።
በህገመንግስቱ መሰረት ማድሪድ ካታሎኒያን ቀጥታ ማስተዳደር ከጀመረች የግዛቲቱን ፋይናንስ፣ ፖሊስ እና መገናኛ ብዙሃንን ትቆጣጠራለች።
ለበለጠ መረጃ Joni us telgram

https://t.me/joinchat/AAAAAER5WRRPcCtY9vBrXA
በስፔን የካታሎኒያ ግዛት ፓርላማ ግዛቲቱ ነፃ አገር መሆኗን ማወጁን ተከትሎ የአገሪቱ ሴኔት ግዛቲቱ ቀጥታ በማድሪድ እንድትተዳደር ወሰነ። 135 መቀመጫ ባለው የካታሎኒያ ፓርላማ 70 አባላት ግዛቲቱ ከስፔን ተገንጥላ ነፃ አገር እንድትሆን የቀረበውን ሞሽን ሲደግፉ፥ 10 ደግሞ ተቃውመዋል። የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪያኖ ራጆይ ከፓርላማው ውሳኔ በኋላ ስፔናውያን እንዳይደናገጡ እና እንዲረጋጉ አሳስበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ ሴኔት ፊት ቀርበው የካታሎኒያ ግዛት ቀጥታ በማድሪድ እንድትተዳደር ያቀረቡት ጥያቄ ፀድቋል። አሁን ያለውን የካታሎኒያ አስተዳደር ቤተሰብን እየከፋፈለ እና ማህበረሰብን እየሰነጣጠቀ ያለ ብለውም ነበር የከሰሱት። በዚህ ብዙ ሰዎች ተሰቃይተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ራጆይ፥ ሁኔታው በንግድ ሰዎች ዘንድ መተማመንን አጥፍቶ ከግዛቲቱ እንዲወጡ እያደረገ መሆኑን ነው ያመለከቱት። የስፔን ህገመንግስት በቀውስ ወቅት ግዛቲቱን ቀጥታ በቁጥጥሩ ስር አድርጎ እንዲያስተዳደር የሚፈቅድ አንቀፅን ያካተተ ሲሆን፥ ሴኔቱ ይህ አንቀፅ እንዲተገበር ነው የወሰነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔያቸውን ሰብስበው በቀጣይ እርምጃ ላይ ይመክራሉ ተብሏል። በህገመንግስቱ መሰረት ማድሪድ ካታሎኒያን ቀጥታ ማስተዳደር ከጀመረች የግዛቲቱን ፋይናንስ፣ ፖሊስ እና መገናኛ ብዙሃንን ትቆጣጠራለች። ለበለጠ መረጃ Joni us telgram https://t.me/joinchat/AAAAAER5WRRPcCtY9vBrXA
0 Comments 0 Shares