ከእቴጌ ጣይቱ ታላቅ ሃሳቦች አንዱ- "የኢትዮጵያ ልማት ባንክ"
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባንክን “ባንክ ኦፍ አብሲኒያ" የተባለውን ባንክ ያቋቋሙት እንግሊዞች ባንኩን በማስተዳደር አገልግሎት ሲሰጡ ከባንኩ ለሥራ ማስኬጃ ሚሆን ገንዘብ የተበደሩ አብዛኛዎቹ የባንኩ ደንበኞች በባንኩ በበለእዳነት እየከሰሳቸው ፍርድ ቤት እየቀረቡ በማስፈረድ ንብረታቸውን እየወረሰ ና ባለዕዳዎቹንም ለእስር እየዳረገ ነበር፡፡ ይህንን የሰሙትና በዚህም ምክንያት ብዙ ሕዝብ በኀዘን ና በለቅሶ ላይ ያለ መሆኑን ያረጋገጡት እቴጌ ጣይቱ ብጡል የባንኩን አሰራር አበሳጭቷቸው ምን ማድረግ እንዳለበቸው ሲያወጡ ሲያወረዱ ከቆዩ በኋላ የበኩላቸውን የመፍትሄ እርምጃዎች ለመውሰድ መንቀሳቅስ ጀመሩ፡፡
አንድ ቀን በቤተመንግስቱ እልፍኝ ምኒልክ ና ሹማምንቶቻቸው በሙሉ በተሰበሰቡበት ስለ "ባንክ ኦፍ አብሲኒያ " ተነስቶ ሲወያዩ ጣይቱ "በመናገሻ ከተማችን ሕዝባችንን እስር ቤት አዘጋጅቶ አይናችን እያየ ፤ጆራችን እየሰማ የእንግሊዝ መንግስት እንዲህ ሲሰራ ይህ ሕዝብ ምኑ የእኛ ነው ማለት ይቻላል? እነዚህ ባለዕዳ ተብለው ፍዳቸውን የሚያዩ ሰዎቻችንን ዕዳቸውን የሚከፍሉበት ዕድል ልንፈጥርላቸው አይገባንምምን?" ሲሉ ሃሳቡን ለውይይት በመሰንዘር ምንልክ ና ሹማምንቶቻቸው እንዲያስቡበት አደረጉ ፡፡
እቴጌ ጣይቱ ብጡል ለችግሩ መፍትሄ ሲያስቡ ቆይተው የእርሻ ና ንግድ ልማት ማስፋፊያ ማህበር (ባንክ) በሚል ስያሜ እንዲቋቋም ለምኒልክ ሐሳብ አቅርበው ስለተፈቀደላቸው የመጀመሪያውን 100,000 ብር እቴጌ ጣይቱ ፣አፄ ምኒልክ ደግሞ 200 ሺ ብር ከመንግሰት ግምጃ ቤት እንዲወጣ አድርገው ሌላውን አክስዮኝ ደግሞ ንጉስ ወልደጊዮርጊስ፣ራስ ተሰማ ሌሎችም የመንግሰት ሹማምንት ና ታዋቂ የሮዘንደር ነጋዴዎች እንዲያዋጡ ፡፡የቀረውን ደግሞ ሕዝቡና መሳፍንቱ እንዲያዋጣ በማድረግ በሴፕቴምበር 2 ቀን 1909 ባንኩ እንዲቋቋም ናሥራ እንዲጀምር ሆነ፡፡
ባንኩ ሥራውን እንደጀመረ በእንግሊዞች ቁጥጥር ስር የሚገኘው "ባንክ ኦፍ አቢሲኒያ" በእዳ ምክንያት ያሰረቸውን ሰዎች ገንዘብ በማበደር የነበረባቸውን እዳ ከፍለው ነጻነታቸው እንዲያገኙ አደረጉ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ባንኩ ንግድ ና እርሻ እቅዶችን ማስፋፊያ አላማ የሚውል ብድር በመስጠት የሕዝቡን ኢኮኖሚ አቅም ለማበልጸግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ፡፡
ይህ በአሁኑ ወቅት "የኢትዮጵያ ልማት ባንክ" በመባል የሚታወቀው መንግስታዊ ባንክ መሰረት የሆነው የእርሻ ና ንግድ ልማት ማስፋፊያ ባንክ የመጀመሪያ ሥራ አስኪጅ ነጋድረስ በሐብቴ ፣በመቀጠልም አቶ ምትኬ ና በመጨረሻም አቶ ይታጠቁ የተባሉ ሥራ አስኪያጆችን እቴጌይቱ ሾመው ነበር፡፡
Xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxx
በጋዜጠኛ ብሩክ መኰንን የተጻፈው "እቴጌ ጣይቱ ብርሃነ ዘ-ኢትዮጵያ" መጽሃፍ
ከእቴጌ ጣይቱ ታላቅ ሃሳቦች አንዱ- "የኢትዮጵያ ልማት ባንክ" በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባንክን “ባንክ ኦፍ አብሲኒያ" የተባለውን ባንክ ያቋቋሙት እንግሊዞች ባንኩን በማስተዳደር አገልግሎት ሲሰጡ ከባንኩ ለሥራ ማስኬጃ ሚሆን ገንዘብ የተበደሩ አብዛኛዎቹ የባንኩ ደንበኞች በባንኩ በበለእዳነት እየከሰሳቸው ፍርድ ቤት እየቀረቡ በማስፈረድ ንብረታቸውን እየወረሰ ና ባለዕዳዎቹንም ለእስር እየዳረገ ነበር፡፡ ይህንን የሰሙትና በዚህም ምክንያት ብዙ ሕዝብ በኀዘን ና በለቅሶ ላይ ያለ መሆኑን ያረጋገጡት እቴጌ ጣይቱ ብጡል የባንኩን አሰራር አበሳጭቷቸው ምን ማድረግ እንዳለበቸው ሲያወጡ ሲያወረዱ ከቆዩ በኋላ የበኩላቸውን የመፍትሄ እርምጃዎች ለመውሰድ መንቀሳቅስ ጀመሩ፡፡ አንድ ቀን በቤተመንግስቱ እልፍኝ ምኒልክ ና ሹማምንቶቻቸው በሙሉ በተሰበሰቡበት ስለ "ባንክ ኦፍ አብሲኒያ " ተነስቶ ሲወያዩ ጣይቱ "በመናገሻ ከተማችን ሕዝባችንን እስር ቤት አዘጋጅቶ አይናችን እያየ ፤ጆራችን እየሰማ የእንግሊዝ መንግስት እንዲህ ሲሰራ ይህ ሕዝብ ምኑ የእኛ ነው ማለት ይቻላል? እነዚህ ባለዕዳ ተብለው ፍዳቸውን የሚያዩ ሰዎቻችንን ዕዳቸውን የሚከፍሉበት ዕድል ልንፈጥርላቸው አይገባንምምን?" ሲሉ ሃሳቡን ለውይይት በመሰንዘር ምንልክ ና ሹማምንቶቻቸው እንዲያስቡበት አደረጉ ፡፡ እቴጌ ጣይቱ ብጡል ለችግሩ መፍትሄ ሲያስቡ ቆይተው የእርሻ ና ንግድ ልማት ማስፋፊያ ማህበር (ባንክ) በሚል ስያሜ እንዲቋቋም ለምኒልክ ሐሳብ አቅርበው ስለተፈቀደላቸው የመጀመሪያውን 100,000 ብር እቴጌ ጣይቱ ፣አፄ ምኒልክ ደግሞ 200 ሺ ብር ከመንግሰት ግምጃ ቤት እንዲወጣ አድርገው ሌላውን አክስዮኝ ደግሞ ንጉስ ወልደጊዮርጊስ፣ራስ ተሰማ ሌሎችም የመንግሰት ሹማምንት ና ታዋቂ የሮዘንደር ነጋዴዎች እንዲያዋጡ ፡፡የቀረውን ደግሞ ሕዝቡና መሳፍንቱ እንዲያዋጣ በማድረግ በሴፕቴምበር 2 ቀን 1909 ባንኩ እንዲቋቋም ናሥራ እንዲጀምር ሆነ፡፡ ባንኩ ሥራውን እንደጀመረ በእንግሊዞች ቁጥጥር ስር የሚገኘው "ባንክ ኦፍ አቢሲኒያ" በእዳ ምክንያት ያሰረቸውን ሰዎች ገንዘብ በማበደር የነበረባቸውን እዳ ከፍለው ነጻነታቸው እንዲያገኙ አደረጉ፡፡ከዚህም በተጨማሪ ባንኩ ንግድ ና እርሻ እቅዶችን ማስፋፊያ አላማ የሚውል ብድር በመስጠት የሕዝቡን ኢኮኖሚ አቅም ለማበልጸግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ፡፡ ይህ በአሁኑ ወቅት "የኢትዮጵያ ልማት ባንክ" በመባል የሚታወቀው መንግስታዊ ባንክ መሰረት የሆነው የእርሻ ና ንግድ ልማት ማስፋፊያ ባንክ የመጀመሪያ ሥራ አስኪጅ ነጋድረስ በሐብቴ ፣በመቀጠልም አቶ ምትኬ ና በመጨረሻም አቶ ይታጠቁ የተባሉ ሥራ አስኪያጆችን እቴጌይቱ ሾመው ነበር፡፡ Xxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxxx በጋዜጠኛ ብሩክ መኰንን የተጻፈው "እቴጌ ጣይቱ ብርሃነ ዘ-ኢትዮጵያ" መጽሃፍ
Like
2
0 Comments 0 Shares