አህያውን ፈርቶ ዳውላውን፡፡ በገዛ ምድራቸው ገዝተዋቸው፣ ጨቁነዋቸው፣ በዝብዘዋቸው ሳያበቁ አሁንም የሀገሪቱን ዋነኛ ኢኮኖሚ በእጃቸው ይዘው የኢኮኖሚ ባሪያ ያደረጓቸው አናሳ ነጮችን አንዲት ነገር የማድረግ ድፍረት ሳይኖራቸው፤ ተቸግሮ የመጣ፣ እነሱ የተዉትን ‹ዝቅተኛ› ስራ ሰርቶ ለመለወጥ የሚሞከረውን የትግል አጋር ጥቁር ወገናቸውን ‹ስራ ተሻማን› በሚል ሰበብ መግደል ምንኛ መታወር ነው? ምንኛ በፍርሃት ቆፈን መያዝ ነው? ምንኛ አለመታደል ነው? መታወር ባይሆንማ ኖሮ ዳቦን አስቀምቶ የዳቦ ፍርፋሪ ላይ ማላዘን ባልኖረ፤ በፍርሃት ቆፈን መያዝ ባይሆንማ ኖሮ ዳቦ ቀሚ ጉልቤን ትቶ የዳቦ ፍርፋሪ ለቃሚ ድንቢጥ ላይ መደንፋት ባልነበረ፤ አለመታደል ባይሆንማ ኖሮ ወገን በወገኑ ባልተነሳ ነበር፡፡

0 Comments 0 Shares