ስለ ህይወት ያለኝን አመለካከት በድጋሚ ላጋራችሁ...
"ህይወት ለኔ ቀልድ ናት። ለዛ ነው አምርሬ የማልኖራት።
የህይወት አላማ የደስታ ስሜት እርካታ ነው። አንድ ሠው
መኪና የሚገዛው መኪናው በራሱ አላማው ሆኖ አይደለም።
መኪናው የጉዞ ስቃይ መቀነሻ ሂደት ነው። የስሜት ለውጥ
እንጂ የህይወት እውነት የለም። ህይወት የግርድፍ ስሜት
እውነታ ናት ። እውነቷ የሚታወቀው በጊዜና ቦታ ሂደት
ድርጊትን በማምታት ለሰው ደስታ በሚፈጠር ሁኔታ ነው። ክፉ
ሁኔታ፣ መልካም ሁኔታ በገሀዱ የሉም። ሁሉም ምንም ነው።
የደስታና የክፋት ሁኔታ የሚፈጠረው በሰው ልጅ የስሜት ዋጋ
ነው። የህይወት ዋጋ ኑሮ ላይ ሳይሆን ነዋሪው ላይ ነው።
አንተ ለወርቅ ዋጋ ካልሰጠኸው ወርቅ በራሱ ምንም ነው።
ውድ የሚሆነው አንተ የስሜት ዋጋ ስትሰጠው ነው። ሁሉንም
ንቀህ ዋጋ ስታሳጠው ህይወት ላንተ የቀልድ
ህልውና ነው። በህይወት ቀልድ አምርሮ መደሰት ትርፉ በሳቅ
መፈንዳት ነው!"
# ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
ስለ ህይወት ያለኝን አመለካከት በድጋሚ ላጋራችሁ... "ህይወት ለኔ ቀልድ ናት። ለዛ ነው አምርሬ የማልኖራት። የህይወት አላማ የደስታ ስሜት እርካታ ነው። አንድ ሠው መኪና የሚገዛው መኪናው በራሱ አላማው ሆኖ አይደለም። መኪናው የጉዞ ስቃይ መቀነሻ ሂደት ነው። የስሜት ለውጥ እንጂ የህይወት እውነት የለም። ህይወት የግርድፍ ስሜት እውነታ ናት ። እውነቷ የሚታወቀው በጊዜና ቦታ ሂደት ድርጊትን በማምታት ለሰው ደስታ በሚፈጠር ሁኔታ ነው። ክፉ ሁኔታ፣ መልካም ሁኔታ በገሀዱ የሉም። ሁሉም ምንም ነው። የደስታና የክፋት ሁኔታ የሚፈጠረው በሰው ልጅ የስሜት ዋጋ ነው። የህይወት ዋጋ ኑሮ ላይ ሳይሆን ነዋሪው ላይ ነው። አንተ ለወርቅ ዋጋ ካልሰጠኸው ወርቅ በራሱ ምንም ነው። ውድ የሚሆነው አንተ የስሜት ዋጋ ስትሰጠው ነው። ሁሉንም ንቀህ ዋጋ ስታሳጠው ህይወት ላንተ የቀልድ ህልውና ነው። በህይወት ቀልድ አምርሮ መደሰት ትርፉ በሳቅ መፈንዳት ነው!" # ደራሲ ይስማዕከ ወርቁ
0 Comments 0 Shares