ከጣና ሃይቅ እስከ ጭስ አባይ ፏፏቴ ባለው የአባይ ወንዝ ዳርቻ ላይ ዓለም አቀፍ የማራቶን መሮጫ ሊሰራ ነው፡፡ ናይል ማራቶን የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የመሮጫ ስፍራ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ለሚደረግ የማራቶን ሩጫ ውድድር እንዲያገለግል ታስቦ የሚሰራ ሲሆን የዲዛይን ጥናቱን ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን አባ የአርክቴክት ስራዎች ድርጅት ማጠናቀቁን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አዲስ አዱኛ ተናግረዋል፡፡
ናይል ማራቶን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ወደ ባህርዳር ከተማ የሚመጡ ቱሪስቶችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ማራቶንን ጨምሮ በረጅም ርቀት የሩጫ ውድድር የሚታወቁ አትሌቶች ባለቤት ብትሆንም ለማራቶን የመሮጫ ስፍራ ባለመኖሩ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እያገኘች እንዳልሆነ የሚያብራሩት ስራ አስኪያጁ አቶ አዲስ ስራው በሚከናወንበት የወንዙ ዳርቻ እና በአጠቃላይ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ብርቅዬ እንስሳትን ለመጎብኘት እድል የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሩጫው የሚጀመርበት የጣና ሃይቅ ዳርቻና የሚጠናቀቅበት የጭስ አባይ ፏፏቴ ልዩ መስህብ ያላቸው ስፍራዎች በመሆናቸው ተሳታፊዎች ውድድሩን የበለጠ እንዲወዱት የሚያደርግ ቦታ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ የባህርዳር ከተማ ከንቲባም በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት ለከተማዋ የበለጠ ድምቀት የሚሰጥ እና በቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ለማግኘት የሚረዳ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም ልዩ ልዩ ዘመናዊ ድልድዮችም የግንባታው አካል እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፡ዛሚ ኤፍኤም
ከጣና ሃይቅ እስከ ጭስ አባይ ፏፏቴ ባለው የአባይ ወንዝ ዳርቻ ላይ ዓለም አቀፍ የማራቶን መሮጫ ሊሰራ ነው፡፡ ናይል ማራቶን የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የመሮጫ ስፍራ በሀገር አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ለሚደረግ የማራቶን ሩጫ ውድድር እንዲያገለግል ታስቦ የሚሰራ ሲሆን የዲዛይን ጥናቱን ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን አባ የአርክቴክት ስራዎች ድርጅት ማጠናቀቁን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አዲስ አዱኛ ተናግረዋል፡፡ ናይል ማራቶን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ወደ ባህርዳር ከተማ የሚመጡ ቱሪስቶችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ማራቶንን ጨምሮ በረጅም ርቀት የሩጫ ውድድር የሚታወቁ አትሌቶች ባለቤት ብትሆንም ለማራቶን የመሮጫ ስፍራ ባለመኖሩ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እያገኘች እንዳልሆነ የሚያብራሩት ስራ አስኪያጁ አቶ አዲስ ስራው በሚከናወንበት የወንዙ ዳርቻ እና በአጠቃላይ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ብርቅዬ እንስሳትን ለመጎብኘት እድል የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሩጫው የሚጀመርበት የጣና ሃይቅ ዳርቻና የሚጠናቀቅበት የጭስ አባይ ፏፏቴ ልዩ መስህብ ያላቸው ስፍራዎች በመሆናቸው ተሳታፊዎች ውድድሩን የበለጠ እንዲወዱት የሚያደርግ ቦታ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ የባህርዳር ከተማ ከንቲባም በበኩላቸው ይህ ፕሮጀክት ለከተማዋ የበለጠ ድምቀት የሚሰጥ እና በቱሪዝም ዘርፍ ገቢ ለማግኘት የሚረዳ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ለማከናወን በዝግጅት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም ልዩ ልዩ ዘመናዊ ድልድዮችም የግንባታው አካል እንደሚሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ምንጭ፡ዛሚ ኤፍኤም
Like
1
0 Comments 0 Shares