አልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ዘመናዊ የዓይን ሆስፒታል ሊገነባ ነው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር አክሊሉ ኃ/ሚካኤል ከአልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።
ሳውዲ በቀል የሆነው አልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን በ678 ሚሊዬን 780 ሽህ ብር በኢትዮጵያ ዘመናዊ የዓይን ሆስፒታል እና ማስልጠኛ ማዕከል ሊገነባ ነው። የሆስፒታሉ መገንባት የአገሪቱን ጤና ዘርፍ እና የዕውቀት ሽግግር እንደሚያሳድግ ተገልጿል።
ዶ/ር አክሊሉ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት ፣ በጎአድራጎት ድርጅቱ ከዚህ በፊት በተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች ላደረገው የህክምና ድጋፍ አመስግነው፣ ድርጅቱ ዘመናዊ የዓይን ሆስፒታል እና ማስልጠኛ ማዕከል መገንባቱ በጤና ዘርፍ ያለውን ስራ ይደግፋል ብለዋል።በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሆስፒታሎች ጋር በመስራት በዘርፉ ያለውን የዕውቀት ሽግግር እና የሠው ሀብት ልማት እንደሚያሳድግ ገልፀዋል።