ሁሉም የሆነው ለበጎ ነው፦
===================
አንድ ቀን የሆነች ሴት ወደ ነብዩ ዳውድ እያለቀሰች መጣችና እንዲህ አለቻቸው
አንተ የአላህ ነብይ ሆይ! ጌታህ ፍትሃዊ ነው ወይስ በዳይ?
እርሳቸውም፦ በአላህ እጠብቃለሁ ምንድነው የምትይው አሏት?
ምን እንደደረሰብኝ ተመልከት እያለች ችግሯን ማውራት ጀመረት,, እኔ ህፃናት ልጆች አሉኝ ፈትል ፈትየ ሽጬ ነው የምመግባቸው ፈትየ በቀይ ፎጣ ጠቅልዬ ለመሸጥ ወደ ሱቅ ስሄድ በድንገት ከላይ ትልቅ አሞራ መጣና ፈትሌን ይዞብኝ ሄደ ብላ የደረሳባትን ነገረቻቸው። ነብዩላህ ዳውድም አንቺ የአላህ ባሪያ! አላህን ፍሪ ታገሽም እያሉ ያፅናኗታል
በድንገት በከተማዋ አሉ የተባሉ አስር ነጋዴዎች ገቡና አንተ ነብይ ሆይ እያንዳንዳችን 100 ዲናር ምፅዋት ልናደርግ ነው የወደዱትን ነገር ያድርጉ አሏቸው። ነብዩ ዳውድም ለምን እንደሚያደርጉ ጠየቁ
እነሱም ፡-ጀልባ ላይ ነበርን ጀልባዋ ተቀደደች ልንሰምጥ ስንል አንድ አሞራ መጣና የሆነ ፎጣ ጣለልን በዛም ፎጣ ቀዳዳውን ደፈነው፡፡ እኛም ከዚህ ነፃ ከወጣን እያንዳንዱ 100 ዲናር ምፅዋት ሊሰጥ ቃል ገብተን ነበርና አመጣን አሉ፡፡
ነብዩ ዳውድም የተሰበሰበውን 1000 ዲናር አንሰተው ለሷ ሰጧትና በየብስና በባህር የሚመግበውን ጌታሽን በዚህ መልኩ ትገልጭዋለሽ በይ ይኸንን ይዘሽ ሂጂ አሏት ፡፡

እኛ ሲሳያችን እንዴት ማግኘት እዳንለብን እናስባለን አላህ ደግሞ ባላሰብነው መልኩ ይመግበናል!!
አላህ መልካም የሆነን ሲሳይን ይስጠን,,, አሚን
ሁሉም የሆነው ለበጎ ነው፦ =================== አንድ ቀን የሆነች ሴት ወደ ነብዩ ዳውድ እያለቀሰች መጣችና እንዲህ አለቻቸው አንተ የአላህ ነብይ ሆይ! ጌታህ ፍትሃዊ ነው ወይስ በዳይ? እርሳቸውም፦ በአላህ እጠብቃለሁ ምንድነው የምትይው አሏት? ምን እንደደረሰብኝ ተመልከት እያለች ችግሯን ማውራት ጀመረት,, እኔ ህፃናት ልጆች አሉኝ ፈትል ፈትየ ሽጬ ነው የምመግባቸው ፈትየ በቀይ ፎጣ ጠቅልዬ ለመሸጥ ወደ ሱቅ ስሄድ በድንገት ከላይ ትልቅ አሞራ መጣና ፈትሌን ይዞብኝ ሄደ ብላ የደረሳባትን ነገረቻቸው። ነብዩላህ ዳውድም አንቺ የአላህ ባሪያ! አላህን ፍሪ ታገሽም እያሉ ያፅናኗታል በድንገት በከተማዋ አሉ የተባሉ አስር ነጋዴዎች ገቡና አንተ ነብይ ሆይ እያንዳንዳችን 100 ዲናር ምፅዋት ልናደርግ ነው የወደዱትን ነገር ያድርጉ አሏቸው። ነብዩ ዳውድም ለምን እንደሚያደርጉ ጠየቁ እነሱም ፡-ጀልባ ላይ ነበርን ጀልባዋ ተቀደደች ልንሰምጥ ስንል አንድ አሞራ መጣና የሆነ ፎጣ ጣለልን በዛም ፎጣ ቀዳዳውን ደፈነው፡፡ እኛም ከዚህ ነፃ ከወጣን እያንዳንዱ 100 ዲናር ምፅዋት ሊሰጥ ቃል ገብተን ነበርና አመጣን አሉ፡፡ ነብዩ ዳውድም የተሰበሰበውን 1000 ዲናር አንሰተው ለሷ ሰጧትና በየብስና በባህር የሚመግበውን ጌታሽን በዚህ መልኩ ትገልጭዋለሽ በይ ይኸንን ይዘሽ ሂጂ አሏት ፡፡ እኛ ሲሳያችን እንዴት ማግኘት እዳንለብን እናስባለን አላህ ደግሞ ባላሰብነው መልኩ ይመግበናል!! አላህ መልካም የሆነን ሲሳይን ይስጠን,,, አሚን
0 Comments 0 Shares