እስፖርት ጀምረናል
እስፖርት ጀምረናል! «ዘውድአለም ታደሰ»
ዛሬ ለምን እንደሁ እንጃ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ስገላበጥ አላሁ አክበር አለ! ቢቸግረኝ በስንት ዘመኔ የሰቀልኩትን ቁምጣ አውርጄ ታጠቅሁ ፥ ሸራ ጫማ ፣ ጋምባሌ ፣ ጓንት ፣ የሹራብ ኮፍያ ..... ዎክማኔንም አነሳሁ። ሞቅ ያለ የእንግሊዝኛ ሙዚቃ በመክፈት ጆሮዬ ላይ ሰካሁ! በቃ ትንሽ ወደፊት ቀደም ከሚለው ቦርጬ ውጪ ደምበኛ ስፖርተኛ መስያለሁ! :)
አላማዬ አጭርና ግልፅ ነው! ጠንክሬ በሚቀጥለው ኦሎምፒክ ለዚች ጎድቋላ ሐገር በመቶ ፣ በሁለት መቶ ፣ በአራትና በስምንት መቶ ፣ በሺህ አምስት መቶ ፣ ብቻ በሁሉም ርቀት ተወዳድሬ ወርቅ ማምጣት ነው! በአሎሎ...