የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ እንዲያነበው አይመከርም)፡ሰላም ነው ጋይስ?! ዛሬ እና በተከታታይ በሚመጡት ቀናት ስለ አራዶች እንጫወታለን፡፡አቦ አራዳ ሳይ ደስ ይለኛል እኮ!ግራጫ ቃጭሎች ላይ ያለው "መዝጌ" እንዴት አራዳ እንደሚወድ ትዝ አላችሁ?!…."እንግዲህ አራዳ ማን ነው?!" ነው ዋናው ጥያቄ መቼም!..."አራዳ" ጥንታዊ የግእዝ ቃል ሲሆን በግርድፉ "የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ቀጥ ብሎ የሚቆም" እንደማለት ሲሆን የቃሉም አመጣጥ እንስሳት ሁሉ አጎንብሰው ሲሄዱ በነበረበት በኋለኛው ዘመን መጀመሪያ...