አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክ የማራቶን ሩጫ ከሁለት ሰዓት በታች እንዲገባ ለማስቻል ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

ናይክ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለማጠናቀቅ እንደሚቻል ለመሞከርም ሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አትሌቶችን መርጦ ነበር ዝግጅት ሲያደርግ የመነረው።

በሙከራ ሩጫው ላይም ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ኬኒያዊው አትሌት ኤሉዪድ ኪፕቾጌ እና ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ተካፍለዋል።

ሆኖም ግን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ለማግባት የተደረገው ጥረት ለ26 ሰከንድ ብቻ ሳይሳካ ቀርቷል።

በዛሬው እለት የተደረገውን የማራቶን ሩጫ የ32 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ 2 ሰዓት ከ00 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በናይክ የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካትም 26 ሰከንዶች ብቻ ነበር የቀሩት።

ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ እና ኢትዮጵያዊው ሌሊሳ ዴሲሳ ኪፕቾጌን ተከትለው መግባት ችለዋል።

ኤሉድ ኪፕቾጌ በዛሬው እለት የማራቶን ሩጫን ያጠናቀቀበት ሰዓት በዓለም ክበረ ወሰንነት አይመዘገብም የተባለ ሲሆን፥ የማራቶን ሩጫ የዓለም

ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በኬኒያዊው አትሌት ዴኒስ ኬሚዬቶ እጅ ይገኛል።

ውጤቱ በዓለም ክበረ ወሰንነት ባይመዘገብም የ32 ዓመቱ ኪፕቾጌ ሩጫውን ታሪካዊ ብሎታል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 28 ፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታዋቂው የስፖርት ትጥቅ አምራች ናይክ የማራቶን ሩጫ ከሁለት ሰዓት በታች እንዲገባ ለማስቻል ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። ናይክ ማራቶንን ከ2 ሰዓት በታች ለማጠናቀቅ እንደሚቻል ለመሞከርም ሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አትሌቶችን መርጦ ነበር ዝግጅት ሲያደርግ የመነረው። በሙከራ ሩጫው ላይም ኢትዮጵያዊው አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፣ ኬኒያዊው አትሌት ኤሉዪድ ኪፕቾጌ እና ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ ተካፍለዋል። ሆኖም ግን ማራቶንን ከሁለት ሰዓት በታች ለማግባት የተደረገው ጥረት ለ26 ሰከንድ ብቻ ሳይሳካ ቀርቷል። በዛሬው እለት የተደረገውን የማራቶን ሩጫ የ32 ዓመቱ ኬኒያዊ አትሌት ኤሉድ ኪፕቾጌ 2 ሰዓት ከ00 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በመግባት ያጠናቀቀ ሲሆን፥ በናይክ የተቀመጠውን እቅድ ለማሳካትም 26 ሰከንዶች ብቻ ነበር የቀሩት። ኤርትራዊው አትሌት ዘረሰናይ ታደሰ እና ኢትዮጵያዊው ሌሊሳ ዴሲሳ ኪፕቾጌን ተከትለው መግባት ችለዋል። ኤሉድ ኪፕቾጌ በዛሬው እለት የማራቶን ሩጫን ያጠናቀቀበት ሰዓት በዓለም ክበረ ወሰንነት አይመዘገብም የተባለ ሲሆን፥ የማራቶን ሩጫ የዓለም ክብረ ወሰን በ2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በኬኒያዊው አትሌት ዴኒስ ኬሚዬቶ እጅ ይገኛል። ውጤቱ በዓለም ክበረ ወሰንነት ባይመዘገብም የ32 ዓመቱ ኪፕቾጌ ሩጫውን ታሪካዊ ብሎታል። ምንጭ፦ ቢቢሲ
0 Comments 0 Shares