አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲካሄድ ደደቢት እና ሀዋሳ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል።
ደደቢት በአዲስ አበባ ስታዲየም ፋሲል ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል።
ለደደቢት ሁለቱንም ግቦች ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር ለፋሲል ኤደም ኮድዞ ከመረብ አዋህዷል።
ሀዋሳ ከተማም በተመሳሳይ ወልዲያ ከተማን 2 ለ 1 የረታ ሲሆን፥ ፍሬው ሰለሞን እና ጃኮ አራፋት የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል። ለወልዲያ ከሽንፈት ያልታደገችውን ግብ አንዱአለም ንጉሴ ማስቆጠር ችሏል።
አርባ ምንጭ ከተማ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ያለው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል።
ጅማ ላይ ከጅማ አባቡና ጋር ጨዋታውን ያደረገው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሳላዲን ሰይድ በ56ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ አሸንፏል።
በሊጉ 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ተጫውቶ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።
ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተክሉ ተስፋዬ በ27ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ቀዳሚ መሆን ቢችልም ሳሙኤል ሳኑሚ በ48ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናን አቻ አድርጓል።
የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ አዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ወላይታ ዲቻን ያስተናግዳል።
ትናንት በተደረጉ የሊጉ መርሃ ግብሮች መከላከያ ድሬዳዋ ከተማን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ፥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሲዳማ ቡና ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ መጠናቀቁ ይታወሳል።

0 Comments
0 Shares