10 የተሽከርካሪ ምርመራና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ተዘጉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 10 የተሽከርካሪ ምርመራ ተቋማትና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት መዘጋታቸውን የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታውቋል።
ተቋማቱ እንዲዘጉ የተደረገው በአቅም ማነስ፣ ግብአት አለመሟላት እና የስነ ምግባር መጓደል ምክንያት መሆኑንም ባለስልጣኑ ገልጿል።
የትራንስፖርት ባለስልጣን እንዳስታወቀው፥ በአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ፣ በተሽከርካሪ የምርመራ ተቋማት እና የመንጃ ፍቃድ አሰጣጥ ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ኃይለማርያም፥ በየጊዜው ቅሬታ የሚነሳባቸውን ቸግሮች ከግምት ያስገባ የህግ ማሻሻያ እቅድ ተዘጋጅቷል ብለዋል።
በተለይ በየጊዜው የሚደረጉ ቁጥጥሮችን ከማጠናከር እና እርምጃዎችን ከመውሰድ በተጨማሪ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረት ይደረጋል ነው ያሉት።
እስካሁንም ባለስልጣኑ በአቅም ማነስ፣ ግብአት አለመሟላት እና የስነምግባር መጓደል ምክንያት 10 የተሽከርካሪ ምርመራ እና አንድ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት እንዲዘጉ አድርጓል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የአመለካከት ችግርን ለመቅረፍ ከ400 በላይ አሰልጣኝ መምህራን የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ጠቁመዋል።
    
               0 Comments
            
               0 Shares
            
         Amharic
Amharic