የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ሴባስቲያን ዱዳ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ይሆናል።

የፖላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ማመቻቸት የጉብኝታቸው አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ
ጉብኝቱ ፖላንድ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት ከአፍሪካ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንደሚያግዛትም ነው የተነገረው።

ፕሬዚዳንት ዱዳ በኢትዮጵያ የሶሰት ቀናት ቆይታ አንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ በቆይታቸው በፖላንዳውያን የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን ይጎበኛሉ ተብሏል።

ፕሬዚዳንቱ በኢትዮ-ፖሊሽ የንግድ ግንኙነት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ አዲስ አበባ ገቡ አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖላንድ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት አንድሬ ሴባስቲያን ዱዳ በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመና ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ይሆናል። የፖላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሰማሩ ማመቻቸት የጉብኝታቸው አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ ጉብኝቱ ፖላንድ በፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት ከአፍሪካ ድጋፍ ለማሰባሰብ እንደሚያግዛትም ነው የተነገረው። ፕሬዚዳንት ዱዳ በኢትዮጵያ የሶሰት ቀናት ቆይታ አንደሚኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ በቆይታቸው በፖላንዳውያን የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን ይጎበኛሉ ተብሏል። ፕሬዚዳንቱ በኢትዮ-ፖሊሽ የንግድ ግንኙነት ጉባኤ ላይ እንደሚገኙም ተጠቅሷል።
0 Comments 0 Shares