አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት አንድ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታን አስተናግዷል።

በስታድ ሉዊዝ 2ኛ በዘንድሮው ቻምፒየንስ ሊግ በርካታ ጎሎቹን ያስቆጠረው ሞናኮ እና በጠንካራ የተከላካይ ክፍሉ ሁለት ግቦችን ብቻ ያስተናገደው የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ተጫውተዋል።

በጨዋታው የመጀመሪያ 20 ደቂቃዎች ሞናኮዎች ጥሩ የሚባሉ የጎል አጋጣሚዎችን ቢፈጥሩም ወጣቱ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ የአንጋፋውን ግብ ጠባቂ ቡፎንን መረብ መድፈር አልቻለም።

ከመስመር የተሻገሩለትን ኳሶች ወደ ጎል ቢሞክርም ትኩረት የማይለየው ጂያንሉጅ ቡፎን ጎል ከመሆን አድኗቸዋል።

ቢያንኮኔሪዎቹ ከኔፕልስ ባዛወሩት አጥቂያቸው ጎንዛሎ ሄጉዌን የ28ኛ እና 58ኛ ደቂቃ ጎሎች ጨዋታውን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል።

ለጎሎቹ መቆጠር ከባርሴሎና በነጻ ዝውውር ያመጡት የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዳኒ አልቬስ ትልቁን ሚና ተጫውቷል።

አልቬስ ሄጉዌን ጎሎቹን እንዲያስቆጥር ኳሶቹን አመቻችቶ አቀብሎታል።

ከጎሎቹ መቆጠር በኋላ ሞናኮዎች ተጭነው ለመጫዎት ቢሞክሩም ውጤቱን መቀልበስ ተስኗቸው ጨዋታው 2 ለ 0 ተጠናቋል።

የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ቱሪን ላይ ተደርጎ በደርሶ መልስ የሚያሸንፈው ቡድን ለዌልሱ የካርዲፍ ስታዲየም ፍጻሜ ትኬት ይቆርጣል።

በምሽቱ የዩሮፓ ሊግ አንድ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታም ተደርጓል።

በአምስተርዳም አሬና በተደረገው ጨዋታ የቀድሞው የአውሮፓ ሃያል አያክስ አምስተርዳም የፈረንሳዩን ኦሎምፒክ ሊዮንን 4 ለ 1 አሸንፎታል።

ለአያክስ ከቼልሲ በውሰት የሄደው በርትራንድ ትራኦሬ፣ ካስፐር ዶልበርግ እና አሚን ዮንስ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ፥ ማቲው ቫልቡዬና ሊዮንን ከባዶ መሸነፍ ያዳነችውን ጎል ማስቆጠር ችሏል።

የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት በፓርክ ኦሎምፒክ ሊዮን ተደርጎ የደርሶ መልሱ አሸናፊ ለፍሬንድስ አሬናው የፍጻሜ ጨዋታ ይቀርባል።

ዛሬ ምሽት ደግሞ የእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ስፔን አምርቶ ከሴልታ ቪጎ ጋር ይጫወታል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከሰሞኑ በተለየ ዛሬ ጠንካራ ቡድናቸውን ይዘው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል።

ለሳምንታት ከሜዳ ርቀው የቆዩት ተከላካዮቹ ክሪስ ስሞሊንግ እና ፊል ጆንስ ከቡድኑ ጋር ልምምድ የሰሩ ሲሆን፥ ምናልባትም በዛሬው ጨዋታ የመሰለፍ እድል ይኖራቸዋል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም አማካዮቹ ፖል ፖግባ ሁዋን ማታም ከቡድኑ ጋር አብረው ልምምድ ሰርተዋል፤ በእሁዱ ጨዋታ ተጎድቶ የወጣው ተከላካዩ ኤሪክ ቤሊም ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኙ ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻር ማንቼስተር ከሰሞኑ በተሻለ ጠንካራ ሆኖ ይቀርባል እየተባለ ነው።
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት አንድ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ጨዋታን አስተናግዷል። በስታድ ሉዊዝ 2ኛ በዘንድሮው ቻምፒየንስ ሊግ በርካታ ጎሎቹን ያስቆጠረው ሞናኮ እና በጠንካራ የተከላካይ ክፍሉ ሁለት ግቦችን ብቻ ያስተናገደው የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ተጫውተዋል። በጨዋታው የመጀመሪያ 20 ደቂቃዎች ሞናኮዎች ጥሩ የሚባሉ የጎል አጋጣሚዎችን ቢፈጥሩም ወጣቱ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ የአንጋፋውን ግብ ጠባቂ ቡፎንን መረብ መድፈር አልቻለም። ከመስመር የተሻገሩለትን ኳሶች ወደ ጎል ቢሞክርም ትኩረት የማይለየው ጂያንሉጅ ቡፎን ጎል ከመሆን አድኗቸዋል። ቢያንኮኔሪዎቹ ከኔፕልስ ባዛወሩት አጥቂያቸው ጎንዛሎ ሄጉዌን የ28ኛ እና 58ኛ ደቂቃ ጎሎች ጨዋታውን 2 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል። ለጎሎቹ መቆጠር ከባርሴሎና በነጻ ዝውውር ያመጡት የቀኝ መስመር ተከላካዩ ዳኒ አልቬስ ትልቁን ሚና ተጫውቷል። አልቬስ ሄጉዌን ጎሎቹን እንዲያስቆጥር ኳሶቹን አመቻችቶ አቀብሎታል። ከጎሎቹ መቆጠር በኋላ ሞናኮዎች ተጭነው ለመጫዎት ቢሞክሩም ውጤቱን መቀልበስ ተስኗቸው ጨዋታው 2 ለ 0 ተጠናቋል። የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ቱሪን ላይ ተደርጎ በደርሶ መልስ የሚያሸንፈው ቡድን ለዌልሱ የካርዲፍ ስታዲየም ፍጻሜ ትኬት ይቆርጣል። በምሽቱ የዩሮፓ ሊግ አንድ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታም ተደርጓል። በአምስተርዳም አሬና በተደረገው ጨዋታ የቀድሞው የአውሮፓ ሃያል አያክስ አምስተርዳም የፈረንሳዩን ኦሎምፒክ ሊዮንን 4 ለ 1 አሸንፎታል። ለአያክስ ከቼልሲ በውሰት የሄደው በርትራንድ ትራኦሬ፣ ካስፐር ዶልበርግ እና አሚን ዮንስ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ፥ ማቲው ቫልቡዬና ሊዮንን ከባዶ መሸነፍ ያዳነችውን ጎል ማስቆጠር ችሏል። የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት በፓርክ ኦሎምፒክ ሊዮን ተደርጎ የደርሶ መልሱ አሸናፊ ለፍሬንድስ አሬናው የፍጻሜ ጨዋታ ይቀርባል። ዛሬ ምሽት ደግሞ የእንግሊዙ ማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ስፔን አምርቶ ከሴልታ ቪጎ ጋር ይጫወታል። አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከሰሞኑ በተለየ ዛሬ ጠንካራ ቡድናቸውን ይዘው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ይጠበቃል። ለሳምንታት ከሜዳ ርቀው የቆዩት ተከላካዮቹ ክሪስ ስሞሊንግ እና ፊል ጆንስ ከቡድኑ ጋር ልምምድ የሰሩ ሲሆን፥ ምናልባትም በዛሬው ጨዋታ የመሰለፍ እድል ይኖራቸዋል ተብሏል። ከዚህ ባለፈም አማካዮቹ ፖል ፖግባ ሁዋን ማታም ከቡድኑ ጋር አብረው ልምምድ ሰርተዋል፤ በእሁዱ ጨዋታ ተጎድቶ የወጣው ተከላካዩ ኤሪክ ቤሊም ለዛሬው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኙ ገልጸዋል። ከዚህ አንጻር ማንቼስተር ከሰሞኑ በተሻለ ጠንካራ ሆኖ ይቀርባል እየተባለ ነው።
0 Comments 0 Shares