አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ወርሃዊ የሀገራት ደረጃ ኢትዮጵያ በነበረችበት 124ኛ ላይ ተቀመጠች።

ወርሃዊው የፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ባላፈው ወር 20 ደረጃዎችን ማሽቆልቆሏ የሚታወስ ነው፡፡

ፊፋ ባወጣው የወሩ ደረጃም ብራዚል፣ አርጀንቲና እና ጀርመን ካለፈው ወር የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ ባሉበት በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

ከአፍሪካ ግብፅ ቀዳሚ ስትሆን ሴኔጋል እና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን ካሜሩን ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል።

የአፍካ መሪዎቹ ሀገራት ከዓለም በደረጃቸው ቅደም ተከተል መሰረት 19ኛ፣ 30ኛ፣ 33ኛ ላይ ይገኛሉ፡፡

በወሩ ማላዊ 14 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ቀዳሚዋ ስትሆን 114ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

ከፍተኛ የደረጃ ማሻሻል ያሳዩ ሀገራት ደግሞ ማዳጋስካር 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 111ኛ፣ ደቡብ ሱዳን 7 ደረጃዎችን በማሻሻል 146ኛ ደረጃን መያዛቸው በመረጃው ተጠቅሷል።

በደረጃው ግርጌ ላይ ደግሞ አንጉይላ፣ ባህማስ፣ ኤርትራ፣ ጂብራልተር፣ ሶማሊያ እና ቶንጋ ያለምንም ነጥብ 206ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውን ከፊፋ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል (ፊፋ) ወርሃዊ የሀገራት ደረጃ ኢትዮጵያ በነበረችበት 124ኛ ላይ ተቀመጠች። ወርሃዊው የፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ ይፋ ሆኗል። ኢትዮጵያ ባላፈው ወር 20 ደረጃዎችን ማሽቆልቆሏ የሚታወስ ነው፡፡ ፊፋ ባወጣው የወሩ ደረጃም ብራዚል፣ አርጀንቲና እና ጀርመን ካለፈው ወር የደረጃ ለውጥ ሳያደርጉ ባሉበት በቅደም ተከተል ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡ ከአፍሪካ ግብፅ ቀዳሚ ስትሆን ሴኔጋል እና የወቅቱ የአፍሪካ ሻምፒዮን ካሜሩን ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል። የአፍካ መሪዎቹ ሀገራት ከዓለም በደረጃቸው ቅደም ተከተል መሰረት 19ኛ፣ 30ኛ፣ 33ኛ ላይ ይገኛሉ፡፡ በወሩ ማላዊ 14 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል ቀዳሚዋ ስትሆን 114ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ከፍተኛ የደረጃ ማሻሻል ያሳዩ ሀገራት ደግሞ ማዳጋስካር 9 ደረጃዎችን በማሻሻል 111ኛ፣ ደቡብ ሱዳን 7 ደረጃዎችን በማሻሻል 146ኛ ደረጃን መያዛቸው በመረጃው ተጠቅሷል። በደረጃው ግርጌ ላይ ደግሞ አንጉይላ፣ ባህማስ፣ ኤርትራ፣ ጂብራልተር፣ ሶማሊያ እና ቶንጋ ያለምንም ነጥብ 206ኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸውን ከፊፋ ድረ ገጽ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
0 Comments 0 Shares