በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ አሸንፏል

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ አንድ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ባለድል ሆኗል።
በባላይዶስ ስታዲየም የስፔኑ ሴልታቪጎ ከማንቼስተር ዩናይትድ ተጫውተዋል።
በሳምንቱ መጨረሻ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ባደረጉት ጨዋታ፥ በርካታ ተጫዋቾቻቸውን አሳርፈው ወደ ሜዳ የገቡት ሴልታቪጎዎች ያሰቡትን አላሳኩም።
ማንቼስተር ዩናይትዶች በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ መንቀሳቀስ እና የጎል እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ያገኙትን አጋጣሚ መጠቀም አልቻሉ።
በዚህ የጨዋታ ጊዜ ወጣቱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከሳጥን ውጭ የግቡ ማዕዘን ላይ የመታት ኳስ በእለቱ ኮከብ በነበረው ግብ ጠባቂ ሰርጅዮ አልቫሬዝ ጥረት ከሽፋለች።
ከዚህ ባለፈም አማካዮቹ ሄንሪክ ሚኪታሪያን እና ጀሴ ሌንጋርድ ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ወደ ጎል መቀየር አልቻሉም።
ግብ ጠባቂው በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ሶስት ኳሶችን ማዳን ችሏል።
በአንጻሩ ሴልታቪጎዎች በዚህ የጨዋታ ጊዜ የሚያስቆጭ የጎል እድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።
አማካዩ ዋስ ከመሃል የተሻገረለትን ኳስ ነጻ ሆኖ ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ከእረፍት መልስ ባለሜዳዎቹ የተሻለ ወደ ጎል መቅረብ ቢችሉም ያሰቡትን ማሳካት አልቻሉም።
በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ የተወሰደባቸው ማንቼስተር ዩናይትዶች በራሽፎርድ የ67ኛው ደቂቃ ጎል ጨዋታውን 1 ለ 0 መምራት ችለዋል።
ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ዩናይትድ በዚህ አመት ያደረገውን 58ኛ ጨዋታ በድል መወጣት ችሏል።
የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ኦልድትራፎርድ ላይ ተደርጎ በደርሶ መልስ አሸናፊው በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ይቀርባል።
ከትናንት በስቲያ በተደረገ ጨዋታ አምስተርዳም አሬና ላይ አያክስ አምስተርዳም ኦሎምፒክ ሊዮንን 4 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።
በዩሮፓ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ ማንቼስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ አሸንፏል አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ትናንት ምሽት በተደረገ የዩሮፓ ሊግ የግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ አንድ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ባለድል ሆኗል። በባላይዶስ ስታዲየም የስፔኑ ሴልታቪጎ ከማንቼስተር ዩናይትድ ተጫውተዋል። በሳምንቱ መጨረሻ ከአትሌቲክ ቢልባኦ ባደረጉት ጨዋታ፥ በርካታ ተጫዋቾቻቸውን አሳርፈው ወደ ሜዳ የገቡት ሴልታቪጎዎች ያሰቡትን አላሳኩም። ማንቼስተር ዩናይትዶች በመጀመሪያው አጋማሽ የተሻለ መንቀሳቀስ እና የጎል እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ያገኙትን አጋጣሚ መጠቀም አልቻሉ። በዚህ የጨዋታ ጊዜ ወጣቱ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ ከሳጥን ውጭ የግቡ ማዕዘን ላይ የመታት ኳስ በእለቱ ኮከብ በነበረው ግብ ጠባቂ ሰርጅዮ አልቫሬዝ ጥረት ከሽፋለች። ከዚህ ባለፈም አማካዮቹ ሄንሪክ ሚኪታሪያን እና ጀሴ ሌንጋርድ ያገኟቸውን አጋጣሚዎች ወደ ጎል መቀየር አልቻሉም። ግብ ጠባቂው በመጀመሪያ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጎል ሊሆኑ የሚችሉ ሶስት ኳሶችን ማዳን ችሏል። በአንጻሩ ሴልታቪጎዎች በዚህ የጨዋታ ጊዜ የሚያስቆጭ የጎል እድል መፍጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። አማካዩ ዋስ ከመሃል የተሻገረለትን ኳስ ነጻ ሆኖ ቢያገኘውም ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ከእረፍት መልስ ባለሜዳዎቹ የተሻለ ወደ ጎል መቅረብ ቢችሉም ያሰቡትን ማሳካት አልቻሉም። በሁለተኛው አጋማሽ ብልጫ የተወሰደባቸው ማንቼስተር ዩናይትዶች በራሽፎርድ የ67ኛው ደቂቃ ጎል ጨዋታውን 1 ለ 0 መምራት ችለዋል። ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ጎል ሳይቆጠር ዩናይትድ በዚህ አመት ያደረገውን 58ኛ ጨዋታ በድል መወጣት ችሏል። የመልሱ ጨዋታ በቀጣዩ ሳምንት ኦልድትራፎርድ ላይ ተደርጎ በደርሶ መልስ አሸናፊው በግንቦት ወር አጋማሽ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ይቀርባል። ከትናንት በስቲያ በተደረገ ጨዋታ አምስተርዳም አሬና ላይ አያክስ አምስተርዳም ኦሎምፒክ ሊዮንን 4 ለ 1 ማሸነፉ ይታወሳል።
0 Comments 0 Shares