27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል

አዲስ አበባ በ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል።
በርካታ ተመልካቾችን ወደ ሜዳ የሳበው የዘንድሮው አመት ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የአራት ሳምንታት መርሃ ግብሮች ብቻ ይቀሩታል።
ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፥ 8 ሰዓት ከ30 ላይ መከላከያ ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።
10 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ በ24 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል።
ፕሪሚየር ሊጉ እሁድ ሲቀጥል በአዲስ አበባ ስታዲየም 8 ሰዓት ከ30 ደደቢት ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ።
በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ 10 ሰዓት ከ30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ።
በክልል ከተሞች ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን ሲያስተናግድ፥ ሃዋሳ ከተማ ከወልዲያ ከተማ ይጫወታሉ።
ጅማ ላይ ደግሞ ጅማ አባቡና የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማና ወላይታ ዲቻ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል።
ሊጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊሰ በ49 ነጥብ ይመራዋል፥ ሲዳማ ቡና በ46 እንዲሁም ደደቢት በ45 ነጥቦች ይከተላሉ።
ድሬዳዋ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዲስ አበባ ከተማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ።

በዘላለም ተፈሪ
27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል አዲስ አበባ በ፣ ሚያዚያ 27 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) 27ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ነገ በሁለት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይውላል። በርካታ ተመልካቾችን ወደ ሜዳ የሳበው የዘንድሮው አመት ፕሪሚየር ሊግ ሊጠናቀቅ የአራት ሳምንታት መርሃ ግብሮች ብቻ ይቀሩታል። ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ሲደረጉ፥ 8 ሰዓት ከ30 ላይ መከላከያ ከድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ። 10 ሰዓት ከ30 ላይ ደግሞ በ24 ነጥብ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል። ፕሪሚየር ሊጉ እሁድ ሲቀጥል በአዲስ አበባ ስታዲየም 8 ሰዓት ከ30 ደደቢት ከፋሲል ከነማ ይጫወታሉ። በሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ 10 ሰዓት ከ30 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጵያ ቡና ይገናኛሉ። በክልል ከተሞች ደግሞ አርባ ምንጭ ከተማ በሜዳው አዳማ ከተማን ሲያስተናግድ፥ ሃዋሳ ከተማ ከወልዲያ ከተማ ይጫወታሉ። ጅማ ላይ ደግሞ ጅማ አባቡና የሊጉን መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስን የሚገጥምበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የ27ኛው ሳምንት መርሃ ግብር የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ በአዲስ አበባ ከተማና ወላይታ ዲቻ መካከል በአዲስ አበባ ስታዲየም ይደረጋል። ሊጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊሰ በ49 ነጥብ ይመራዋል፥ ሲዳማ ቡና በ46 እንዲሁም ደደቢት በ45 ነጥቦች ይከተላሉ። ድሬዳዋ ከተማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዲስ አበባ ከተማ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ። በዘላለም ተፈሪ
0 Comments 0 Shares