በእህቴ ሰርግ ላይ እንዴት እንደዛ ብለው
ይዘፍናሉ.....?
(አሌክስ አብርሃም ላላነበቡት ብቻ)

እህቴ ስታገባ እቤታችን ሰርግ ተደግሶ
ነበር፡፡ ያውም ድል ያለ ሰርግ ፡፡ ለመጀመሪያ
ጊዜ በሰርግ የተደሰትኩት የዛን ጊዜ ነው ፡፡
እህቴን ከነኮተቷ ከቤት የሚወስድ ጅል ሲገኝ
እንዴት አልደሰትም!!
የመንደሩ ሰው ሁሉ ..‹‹.እች ልጅ ቁማ መቅረቷ ነው?..›› እያለ ሲያማት እሷም በሙሉ ሃይሏ
እየዘነጠችና እየተቆነጃጀች (ባል አጥቸ
ሳይሆን የሚመጥነኝ ጠፍቶ ነው) አይነት ጉራ
ቀመስ መልክት እያስተላለፈች
ስትኖር ....በአንድ የተንሸዋረረ ቅዳሜ እህቴ
ባል የሚሆናትን ልጅ አገኘች (ማነው ስሙ አሜሪካንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኝ እንደሷ
አልተደሰተም)፡፡
እንዴት እንደተገኛኙ ባይገባኝም ልክ በወጥመድ
እንደተያዘ ወፍ አጣድፋ ትዳር የሚባል ትልቅ
የብረት ድስት ውስጥ ከተተችው፡፡ እንደዜጋ
ልጁ ቢያሳዝነኝም የእህቴም ችግር ይገባኛልና ‹‹ኧረ አስብበት›› ለማለት አልደፈርኩም፡፡
ሰርጉ ተደገሰ ለእህቴ ሚዜ ለመሆን የአገር
ሴቶች ተሰበሰቡ (አሁን ሚዜ መሆን ምን ያሻማል)
እና ሰርጉ ደርሶ ሚዜ ተብየወቹ ነፍሳቸውን
እስኪስቱ ዘንጠው በቀለም የጥምቀት ዱላ
መስለው .. የገናም አባት መስለው... አበባ አንከርፍፈውና ተራቁተው እግረ ሚዜነታቸውን
ለራሳቸው ከሰርገኛው መሃል ባል እየፈለጉ
እያለ ሙሽራው መጣ (እኔማ ይቀራል ብየ ነበር
የሚገርም ደፋር ነው)
ከመጣም በኋላ ካሁን አሁን ‹‹ይሄ ነገር ሳስበው
ቢቀርብኝ ይሻላል ›› ይላል እያልኩ ስሰጋ ....እነዛ ቀልቃላ ሚዜወቿ ‹‹አናስገባም
ሰርገኛ›› ብለው እርፍ!!....እንዴዴዴዴዴ እች
ልጅ ሚዜ ነው ምቀኛ የሰበሰበችው ብየ የመጨረሻ
ተበሳጨሁ በአእርግጠኝነት ሙሽራው ‹‹ታዲያ የት
ልግባ ቢል›› ሁሉም ሚዜወች ላዳ ተከራይተው
እቤታቸው ነበር የሚወስዱት !! በስንት መከራ የተገኘ ባል ‹‹አናስገባም››! እኔ
ወደፊት ስሞት መላአእክት ወደገነት
‹‹አናስገባም›› ቢሉኝ እራሱ እንደዚያ ቀን
የምደነግጥ አይመስለኝም!! ይታያችሁ እህቴ ባል ለማግባት ለኪዳነ ምህረት
፣ለገብሬል ...ለማሪያም...የተሳለችው መጋረጃ
ቢቀጣጠል አንድ ክፍለ ከተማ
ይጋርዳል ....የተሳለችው ጧፍ የብዙ ደብሮችን
የአመት የጧፍ ፍጆታ ይችላል...እና ሚዜወቿ
‹‹አናስገባም›› እያሉ በእሳት ይጫወታሉ !! አባባ በሩን ለሰርጉ ብሎ ሰፋ ያስደረገው ቶሎ
ይዞልን እንዲሄድ አይደል እንዴ ! ወይ ሚዜ !
ወይ ሴቶች ! ለሞላ ዘፈን
‹‹አናስገባም›› ....ቀስ ብየ ወደዲጀው ጠጋ
አልኩና በጆሮው መፍትሄ ነገር ሹክ አልኩት
‹‹ኧረ አሌክስ ይሄማ አሁን አይከፈትም ሲወጠጡ ነው ›› አለኝ ...አትሸኟትም ወይ የሚለውን
የፀጋየ እሸቱን የሰርግ ዘፈን ነበር ክፈትልን
ያልኩት
በእህቴ ሰርግ ላይ እንዴት እንደዛ ብለው ይዘፍናሉ.....? (አሌክስ አብርሃም ላላነበቡት ብቻ) እህቴ ስታገባ እቤታችን ሰርግ ተደግሶ ነበር፡፡ ያውም ድል ያለ ሰርግ ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰርግ የተደሰትኩት የዛን ጊዜ ነው ፡፡ እህቴን ከነኮተቷ ከቤት የሚወስድ ጅል ሲገኝ እንዴት አልደሰትም!! የመንደሩ ሰው ሁሉ ..‹‹.እች ልጅ ቁማ መቅረቷ ነው?..›› እያለ ሲያማት እሷም በሙሉ ሃይሏ እየዘነጠችና እየተቆነጃጀች (ባል አጥቸ ሳይሆን የሚመጥነኝ ጠፍቶ ነው) አይነት ጉራ ቀመስ መልክት እያስተላለፈች ስትኖር ....በአንድ የተንሸዋረረ ቅዳሜ እህቴ ባል የሚሆናትን ልጅ አገኘች (ማነው ስሙ አሜሪካንን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲያገኝ እንደሷ አልተደሰተም)፡፡ እንዴት እንደተገኛኙ ባይገባኝም ልክ በወጥመድ እንደተያዘ ወፍ አጣድፋ ትዳር የሚባል ትልቅ የብረት ድስት ውስጥ ከተተችው፡፡ እንደዜጋ ልጁ ቢያሳዝነኝም የእህቴም ችግር ይገባኛልና ‹‹ኧረ አስብበት›› ለማለት አልደፈርኩም፡፡ ሰርጉ ተደገሰ ለእህቴ ሚዜ ለመሆን የአገር ሴቶች ተሰበሰቡ (አሁን ሚዜ መሆን ምን ያሻማል) እና ሰርጉ ደርሶ ሚዜ ተብየወቹ ነፍሳቸውን እስኪስቱ ዘንጠው በቀለም የጥምቀት ዱላ መስለው .. የገናም አባት መስለው... አበባ አንከርፍፈውና ተራቁተው እግረ ሚዜነታቸውን ለራሳቸው ከሰርገኛው መሃል ባል እየፈለጉ እያለ ሙሽራው መጣ (እኔማ ይቀራል ብየ ነበር የሚገርም ደፋር ነው) ከመጣም በኋላ ካሁን አሁን ‹‹ይሄ ነገር ሳስበው ቢቀርብኝ ይሻላል ›› ይላል እያልኩ ስሰጋ ....እነዛ ቀልቃላ ሚዜወቿ ‹‹አናስገባም ሰርገኛ›› ብለው እርፍ!!....እንዴዴዴዴዴ እች ልጅ ሚዜ ነው ምቀኛ የሰበሰበችው ብየ የመጨረሻ ተበሳጨሁ በአእርግጠኝነት ሙሽራው ‹‹ታዲያ የት ልግባ ቢል›› ሁሉም ሚዜወች ላዳ ተከራይተው እቤታቸው ነበር የሚወስዱት !! በስንት መከራ የተገኘ ባል ‹‹አናስገባም››! እኔ ወደፊት ስሞት መላአእክት ወደገነት ‹‹አናስገባም›› ቢሉኝ እራሱ እንደዚያ ቀን የምደነግጥ አይመስለኝም!! ይታያችሁ እህቴ ባል ለማግባት ለኪዳነ ምህረት ፣ለገብሬል ...ለማሪያም...የተሳለችው መጋረጃ ቢቀጣጠል አንድ ክፍለ ከተማ ይጋርዳል ....የተሳለችው ጧፍ የብዙ ደብሮችን የአመት የጧፍ ፍጆታ ይችላል...እና ሚዜወቿ ‹‹አናስገባም›› እያሉ በእሳት ይጫወታሉ !! አባባ በሩን ለሰርጉ ብሎ ሰፋ ያስደረገው ቶሎ ይዞልን እንዲሄድ አይደል እንዴ ! ወይ ሚዜ ! ወይ ሴቶች ! ለሞላ ዘፈን ‹‹አናስገባም›› ....ቀስ ብየ ወደዲጀው ጠጋ አልኩና በጆሮው መፍትሄ ነገር ሹክ አልኩት ‹‹ኧረ አሌክስ ይሄማ አሁን አይከፈትም ሲወጠጡ ነው ›› አለኝ ...አትሸኟትም ወይ የሚለውን የፀጋየ እሸቱን የሰርግ ዘፈን ነበር ክፈትልን ያልኩት
0 Comments 0 Shares