ኢንተርፕራይዙ በዘጠኝ ወራት ካቀደው በታች 11.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷል
የአገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ዓለም አቀፍ ባህሮችን የሚያቆራርጠው ግዙፉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፐራይዝ፣ በአገሪቱ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባቀደው መጠን ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ሳይችል ቀረ፡፡
ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሚመራው የኢንተርፐራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ በቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አስመጪዎች በቂ የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸውና የዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመቀዛቀዙ የታሰበውን ያህል አልተሄደም፡፡
በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ኤልሲ (L/C) በበቂ ደረጃ መክፈት ባለመቻሉ፣ ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዙ ባለፉት ዘጠኝ ወራት አገር ውስጥ ለማስገባት ያቀደው 136,116 ኮንቴይነሮችን ቢሆንም፣ በአፈጻጸሙ ግን 131,834 ኮንቴይነሮች ገብተዋል፡፡
በገቢ ረገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢንተርፕራይዙ በአጠቃላይ 14.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ቢያቅድም፣ ማሳካት የቻለው ግን 11.8 ቢሊዮን ብር ነው፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ተፈራ፣ ረቡዕ ሚያዝያ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ 40 ኤጀንቶች ጋር ባካሄዱት ውይይት ወቅት ለጋዜጠኞች እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ኢንቨስትመንት ላይ ያለች አገር ናት፡፡ የምታመነጨው የውጭ ምንዛሪ ውስን እንደመሆኑ ቅድሚያ የሚሰጠው ለተመረጡ ዘርፎች መሆኑን ገልጸው፣ ከዚህ አንፃር የውጭ ምንዛሪ እጥረት በመኖሩ በተለይ በወራት ተከፋፍሎ ሲታይ ባለፈው መጋቢት የገቢ ዕቃ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡ ‹‹በአሁኑ ወቅት ኤልሲ እየተከፈተ በመሆኑ የገቢ ዕቃ ጭማሪ ይኖራል፤›› ሲሉ አቶ መስፍን በቀጣዮቹ ወራት የተሻለ አፈጻጸም ሊኖር እንደሚችል አስረድተዋል፡፡
በሎጂስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የንግዱ ማኅበረሰብ በተያዘው የበጀት ዓመት የውጭ ምንዛሪ በበቂ ደረጃ አላገኘም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2010 በርካታ መርከቦች ተገንብተው አብዛኛዎቹ ወደ ሥራ በመግባታቸው የሥራ ሽሚያ ተከስቷል፡፡ በዚህ ምክንያት የገበያ መቀዛቀዝ ብቻ ሳይሆን፣ የባህር ትራንስፖርት የመጓጓዣ ዋጋ ላይም ቅናሽ እንዲከሰት አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዓለም የንግድ እቅንስቃሴ እየቀዘቀዘ በመሆኑ፣ በርካታ የዘርፉ ተዋናዮች ሥራ እያገኙ አይደለም ሲሉ የወቅቱን ሁኔታ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ የፕላንና ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ሲራጅ አቡዱላሂ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢንተርፕራይዙ ባሉት 11 መርከቦችና ከውጭ በሚከራያቸው መርከቦች በዓለም አቀፍ ደረጃ የባህር ወሽመጦችን እያቋረጠ 309 ወደቦችን ያዳርሳል ብለዋል፡፡ በተለይ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የንግድ መዳረሻ የሆኑት የሩቅ ምሥራቅ አገሮች፣ መካከለኛው ምሥራቅና ቱርክ ዋነኛ መዳረሻዎቹ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
አቶ መስፍን እንዳሉት፣ ኢንተርፕራይዙ ካለፈው ዓመት የተሸጋገሩ ገቢ ዕቃዎች ስለነበሩ በማጓጓዝ በኩል 98 በመቶ፣ በገቢ በኩል ደግሞ ከጂቡቲ ወደብ የሚነሱ ዕቃዎች ስለነበሩ በአጠቃላይ 90 በመቶ አፈጻጸም አስመዝግቧል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ከባህር ጉዞ በተጨማሪ በአገሪቱ በተገነቡ ሰባት ደረቅ ወደቦች 417 ከባድ ተሽከርካሪዎችን በማሰማራት የማጓጓዝ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ታውቋል፡፡

0 Comments
0 Shares