የአፍሪካ የፖለቲካ መዲና በመባል የምትታወቀው አዲስ አበባ ደረጃቸውን የጠበቁ በቂ ሆቴሎች እንደሌላት ሲነገር ቆይቷል። ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ግን በርካታ ሆቴሎች እየተገነቡ በሮቻቸውን ለእንግዶች እየከፈቱ ነው። እንደ አዲስ አበባ ሆቴሎች ማኅበር ገለጻ በየሁለት ወራት ሦስት ሆቴሎች ገበያውን እየተቀላቀሉ
ነው። በአሁኑ ወቅት 52 የሆቴል ፕሮጀክት በሒደት ላይ እንደሆኑ ታውቋል። ወደ ገበያ ለመግባት ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ ሆቴሎች መካከል ሳፋየር አዲስ ሆቴል አንዱ ነው። ሳፋየር አዲስ ሆቴል ቴሌ መድኃኔዓለም አካባቢ በ1,300
ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነው። 130 የመኝታ ክፍሎች፣ ሁለት ሬስቶራንቶች ሦስት ባሮች፣ ጂምናዚየም፣ ስፓና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን አሟልቶ መያዙ ተገልጿል። አቶ ፍስሐ ዓባይ በተባሉ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት የተገነባው
አዲስ ሳፋየር ሆቴል ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል። በምሥሉ ላይ የሚታየው ባለ አሥር ፎቅ ሕንፃ አዲስ ሳፋየር ሆቴል ነው።

0 Comments
0 Shares