ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ
ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ፡፡ሸገር ወሬውን የሰማው መቀመጫቸውን በሪያድ ካደረጉት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ባለሥልጣን አንባሣደር አሚን አቡዱላሂ ነው፡፡

የመከላከያ ሠራዊትን የጨመረው የሳውዲ መንግሥት የህገ-ወጥ የአሰሳ ግብረ-ሃይልን ጨምሮ በገጠር በእርሻ ቦታዎች የሚሰሩ የውጭ ዜጐችን አድኖ የሚይዝና በየቤቱም የተሰማራ ኃይል መቋቋሙን አምባሣደሩ ነግረውናል፡፡የሳውዲ ዜጐች ወረቀት የሌላቸውን የውጭ ሰዎች የሚቀጥሩ ከሆነ ከባድ ቅጣት የሚጥልባቸው አዋጅ ከማውጣቱም በላይ ማረሚያ ቤቱንም እያስፋፋ ነው ተብሏል፡፡

የፖሊስና የማረሚያ ቤት የመከላከያ ሠራዊት አባላቱን ቁጥር ማብዛቱንም አምባሣደር አሚን ነግረውናል፡፡ሳውዲ አረቢያ በቅርቡ ከውጭ ሀገር ዜጐች የፀዳች ሳውዲ የሚለውን ኃሣባቸውን በፓርላማቸው በማፅደቃቸው ወረቀት አልባ ኢትዮጵያዊያን በጉዳዩ ሳይዘናጉ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ብለዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ ሳውዲ አረቢያ በሀገሯ የሚገኙትን ወረቀት አልባ የውጪ ዜጐችን በ3 ወራት ውስጥ ለማስወጣት ከ19 በላይ መንግሥታዊ ተቋሞችን ማዘጋጀቷና ማሰማራቷ ተሠማ፡፡ሸገር ወሬውን የሰማው መቀመጫቸውን በሪያድ ካደረጉት የኢትዮጵያ ባለሙሉ ባለሥልጣን አንባሣደር አሚን አቡዱላሂ ነው፡፡ የመከላከያ ሠራዊትን የጨመረው የሳውዲ መንግሥት የህገ-ወጥ የአሰሳ ግብረ-ሃይልን ጨምሮ በገጠር በእርሻ ቦታዎች የሚሰሩ የውጭ ዜጐችን አድኖ የሚይዝና በየቤቱም የተሰማራ ኃይል መቋቋሙን አምባሣደሩ ነግረውናል፡፡የሳውዲ ዜጐች ወረቀት የሌላቸውን የውጭ ሰዎች የሚቀጥሩ ከሆነ ከባድ ቅጣት የሚጥልባቸው አዋጅ ከማውጣቱም በላይ ማረሚያ ቤቱንም እያስፋፋ ነው ተብሏል፡፡ የፖሊስና የማረሚያ ቤት የመከላከያ ሠራዊት አባላቱን ቁጥር ማብዛቱንም አምባሣደር አሚን ነግረውናል፡፡ሳውዲ አረቢያ በቅርቡ ከውጭ ሀገር ዜጐች የፀዳች ሳውዲ የሚለውን ኃሣባቸውን በፓርላማቸው በማፅደቃቸው ወረቀት አልባ ኢትዮጵያዊያን በጉዳዩ ሳይዘናጉ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ብለዋል፡፡
0 Comments 0 Shares