ፖሊስና ሌባ - አሣየ ደረበ
-
አንደኛ እቅድማ
እንደ እኛ ልጅነት
ግማሻችን ዶክተር
ግማሻችን ፓይለት
እንሆናለን ብለን
እንመኝ ነበረ
እንኳንም ህልማችን
ልጅነት ጋር ቀረ::

ጡንቻችን ሲዳብር
ለአቅመ አሳብ ስንደርስ
ግማሻችን ሌባ
ግማሻችን ፖሊስ
ሳንሆን ብንቀር፤
ሁሉም ፓይለት ሁኖ
ምን እናበር ነበር፡፡
ፖሊስና ሌባ - አሣየ ደረበ - አንደኛ እቅድማ እንደ እኛ ልጅነት ግማሻችን ዶክተር ግማሻችን ፓይለት እንሆናለን ብለን እንመኝ ነበረ እንኳንም ህልማችን ልጅነት ጋር ቀረ:: ጡንቻችን ሲዳብር ለአቅመ አሳብ ስንደርስ ግማሻችን ሌባ ግማሻችን ፖሊስ ሳንሆን ብንቀር፤ ሁሉም ፓይለት ሁኖ ምን እናበር ነበር፡፡
0 Comments 0 Shares