የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔና የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን
ሥራ አመራር ቦርድ ያጸደቁት የከተማዋ የውሃ ታሪፍ ጭማሪ በጠ/ሚ ኃ/
ማሪያም ደሳለኝ ታገደ
~~~~~~~~~~~//~~~~~~~~~~~//~~~~~~~~~~//
~~~~~~~~~~~~~~
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የውኃ ታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ውሳኔ
ቢያሳልፍም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ውሳኔው ተግባራዊ
እንዳይደረግ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተሰማ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ
ባለሥልጣን ሥራ አመራር ቦርድ ለከተማው ነዋሪዎች በሚቀርበው ውኃ ታሪፍ
ላይ ማሻሻያ (ጭማሪ) እንዲደረግ በበጀት ዓመቱ መጀመርያ ውሳኔ አሳልፈው
ነበር፡፡
የታሪፍ ጭማሪው መነሻ የአዲስ አበባ ከተማ የውኃ ታሪፍ ከሌሎች የኢትዮጵያ
ከተሞችና ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ይህ የታሪፍ
ምጣኔ ዝቅተኛ መሆኑ ደግሞ ባለሥልጣኑ ለሚያከናውናቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች
ሁነኛ የፋይናንስ ምንጭ መሆን ባለመቻሉ ነው ተብሏል፡፡
የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች በተለያዩ አማራጮች የታሪፍ ጭማሪ ጥናት ካካሄዱ
በኋላ ማሻሻያው በሥራ አመራር ቦርዱና በካቢኔው ተቀባይነት ቢያገኝም፣
በመጨረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዳይደረግ
መታገዱ ተረጋግጧል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ አወቀ
ኃይለ ማርያም እንደገለጹት፣ የታሪፍ ጭማሪው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት
አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ደረጃ ማድረስ ያስፈልጋል በሚል ምክንያት፣
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭማሪው እንዲዘገይ አድርገዋል፡፡

0 Comments
0 Shares