በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ያሰበውን ያህል ገቢ ዕቃዎች ሳያስገባ ቀረ
ኢንተርፕራይዙ በዘጠኝ ወራት ካቀደው በታች 11.8 ቢሊዮን ብር ገቢ አግኝቷልየአገሪቱን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ ዓለም አቀፍ ባህሮችን የሚያቆራርጠው ግዙፉ የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ኢንተርፐራይዝ፣ በአገሪቱ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባቀደው መጠን ገቢ ዕቃዎችን ማጓጓዝ ሳይችል ቀረ፡፡ሐሙስ ሚያዝያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ለሚመራው የኢንተርፐራይዙ ሥራ አመራር ቦርድ በቀረበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ አስመጪዎች በቂ የውጭ ምንዛሪ ባለማግኘታቸውና የዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ዘርፍ በመቀዛቀዙ የታሰበውን ያህል አልተሄደም፡፡በተለይ የንግዱ ማኅበረሰብ ኤልሲ (L/C) በበቂ