በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው

“በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው ፤ በዚህ ፍጥነት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድን ህንፃ ገንብቶ ሲጠናቀቅ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፤ እኛም ተሳስተን ግን እንጨርሳለን ብለናችሁ ነበር…”የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባግንባታ ላይ ያሉ የ40/60 ቤቶች በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጣቢዎች ይሰጣሉ መባሉ በስህተት የተናገርነው ነው አለ…

እየተገነቡ ነው የተባሉት ከ38 ሺ በላይ የ40/60 ቤቶች መቼ እንደሚጠናቀቁ አይታወቅም፡፡መስተዳደሩ ይህን ያለው ዛሬ በ40/60 ቤቶች የ2009 ዓ.ም አፈፃፀምና የ2010 ዓ.ም የሥራ ዕድቅ ላይ ከኮንትራክተሮች፣ ከአማካሪዎችና ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ባደረገ ጊዜ ነው፡፡የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሣቢና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 መኖሪያ ቤቶች ከውል ውጭ ሰፋፊ ሆነው በስህተት ተሰርተዋል ብለዋል፡፡

በዚህም ሳቢያ ባለ1 መኝታ ቤት የሚባለው ቀርቶ ያልታሰበው ባለ 4 መኝታ ቤት ተገንብቶ እጣ ወጥቶበታል ነው ያሉት፡፡ይሁን እንጂ ቤቶቹ አንዳንድ ክፍል የተጨመረባቸው ለሠራተኛ ተብሎ የተገነቡት ክፍሎች ተጨምረው ነውና ይህ አግባብ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ምክትል ከንቲባው የቤቶቹ ስፋት ጋር አያይዘው ብቻ መልስ ሰጥተዋል፡፡ይህ በአሰራር ሂደት የሚያጋጥምና ወደፊትም በዲዛይን ለውጥ ሳቢያ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳ ቤቶቹ በህዝብ ገንዘብ ጭምር ቢገነቡም ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ አንጠይቅም ብለዋል፡፡
በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው “በግንባታ ላይ ያሉት ቤቶች በሙሉ በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጠባችሁት እንሰጣችኋለን ያልናችሁ በስህተት ነው ፤ በዚህ ፍጥነት በኢትዮጵያ ውስጥ አንድን ህንፃ ገንብቶ ሲጠናቀቅ ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፤ እኛም ተሳስተን ግን እንጨርሳለን ብለናችሁ ነበር…”የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባግንባታ ላይ ያሉ የ40/60 ቤቶች በ18 ወራት ተጠናቀው ለቆጣቢዎች ይሰጣሉ መባሉ በስህተት የተናገርነው ነው አለ… እየተገነቡ ነው የተባሉት ከ38 ሺ በላይ የ40/60 ቤቶች መቼ እንደሚጠናቀቁ አይታወቅም፡፡መስተዳደሩ ይህን ያለው ዛሬ በ40/60 ቤቶች የ2009 ዓ.ም አፈፃፀምና የ2010 ዓ.ም የሥራ ዕድቅ ላይ ከኮንትራክተሮች፣ ከአማካሪዎችና ከሚመለከታቸው ጋር ውይይት ባደረገ ጊዜ ነው፡፡የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሣቢና የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ሲመልሱ በቅርቡ እጣ የወጣባቸው የ40/60 መኖሪያ ቤቶች ከውል ውጭ ሰፋፊ ሆነው በስህተት ተሰርተዋል ብለዋል፡፡ በዚህም ሳቢያ ባለ1 መኝታ ቤት የሚባለው ቀርቶ ያልታሰበው ባለ 4 መኝታ ቤት ተገንብቶ እጣ ወጥቶበታል ነው ያሉት፡፡ይሁን እንጂ ቤቶቹ አንዳንድ ክፍል የተጨመረባቸው ለሠራተኛ ተብሎ የተገነቡት ክፍሎች ተጨምረው ነውና ይህ አግባብ ነው ወይ ? ተብለው የተጠየቁት ምክትል ከንቲባው የቤቶቹ ስፋት ጋር አያይዘው ብቻ መልስ ሰጥተዋል፡፡ይህ በአሰራር ሂደት የሚያጋጥምና ወደፊትም በዲዛይን ለውጥ ሳቢያ ሊያጋጥም የሚችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ምንም እንኳ ቤቶቹ በህዝብ ገንዘብ ጭምር ቢገነቡም ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ አንጠይቅም ብለዋል፡፡
0 Comments 0 Shares