በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ

በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ፡፡ከአንድ ዙር ቅበላው እግድ በተጨማሪ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሰምተናል፡፡የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክት አቶ ፍሬው ተሻለ ለሸገር እንደተናገሩት በአዲስ አበባ 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡

ተቋማቱ የሚሰጡትን የስልጠና አሰጣጥ ለመገምገም የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የማሰልጠኛ ተቋማት ህብረትና የሚገመገሙ ማሰልጠኛ ተቋማት ተወካይ በሚገኙበት ግምገማ ሲካሄድ መክረሙን ነግረውናል፡፡በ66 የአሽከርካሪ ተቋማት ላይ በተደረገው ግምገማም 18ቱ ያለባቸውን ችግሮች እስካስተካከሉ ድረስ የአንድ ዙር ቅበላ እግድና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ሌሎች አራት ተቋማት ደግሞ የሁለት ዙር ቅበላ እንዳያካሄዱና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ፍሬው ተሻለ ነግረውናል፡፡የአንድና የሁለት ዙር ቅበላ እገዳው በየሥልጠና መስኩ እንደሚለያይም ነግረውናል፡፡ግምገማ ከተደረገላቸው ውስጥ 13ቱ ተቋማት ከአነስተኛ ጉድለት ውጪ ጥሩ ናችሁ ተብለዋል፡፡17 ተቋማት ደግሞ የመጀመሪያ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አቶ ፍሬው ነግረውናል፡፡

በተደረገው ግምገማ ለጊዜው የተዘጋ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም የለም ያሉት አቶ ፍሬው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋማት ጉድለታቸውን ካላስተካከሉ ወደ መዝጋት እርምጃ ይገባል ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ባሉት 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የተደረገው ግምገማ የ4 ወር ጊዜ የፈጀ መሆኑንም አቶ ፍሬው ተሻለ ተናግረዋል፡፡

ንጋቱ ሙሉ
በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ በአዲስ አበባ 18 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የአንድ ዙር የሥልጠና ቅበላ እንዳያደርጉ መታገዳቸው ተሠማ፡፡ከአንድ ዙር ቅበላው እግድ በተጨማሪ የመጨረሻ የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ሰምተናል፡፡የባለሥልጣኑ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክት አቶ ፍሬው ተሻለ ለሸገር እንደተናገሩት በአዲስ አበባ 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ይገኛሉ፡፡ ተቋማቱ የሚሰጡትን የስልጠና አሰጣጥ ለመገምገም የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የማሰልጠኛ ተቋማት ህብረትና የሚገመገሙ ማሰልጠኛ ተቋማት ተወካይ በሚገኙበት ግምገማ ሲካሄድ መክረሙን ነግረውናል፡፡በ66 የአሽከርካሪ ተቋማት ላይ በተደረገው ግምገማም 18ቱ ያለባቸውን ችግሮች እስካስተካከሉ ድረስ የአንድ ዙር ቅበላ እግድና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሌሎች አራት ተቋማት ደግሞ የሁለት ዙር ቅበላ እንዳያካሄዱና የመጨረሻ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ፍሬው ተሻለ ነግረውናል፡፡የአንድና የሁለት ዙር ቅበላ እገዳው በየሥልጠና መስኩ እንደሚለያይም ነግረውናል፡፡ግምገማ ከተደረገላቸው ውስጥ 13ቱ ተቋማት ከአነስተኛ ጉድለት ውጪ ጥሩ ናችሁ ተብለዋል፡፡17 ተቋማት ደግሞ የመጀመሪያ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አቶ ፍሬው ነግረውናል፡፡ በተደረገው ግምገማ ለጊዜው የተዘጋ የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም የለም ያሉት አቶ ፍሬው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋማት ጉድለታቸውን ካላስተካከሉ ወደ መዝጋት እርምጃ ይገባል ብለዋል፡፡በአዲስ አበባ ባሉት 66 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ላይ የተደረገው ግምገማ የ4 ወር ጊዜ የፈጀ መሆኑንም አቶ ፍሬው ተሻለ ተናግረዋል፡፡ ንጋቱ ሙሉ
0 Comments 0 Shares