በአቃቂ በበግ ተራ በኩል ያለው የመኪና መተላለፊያ ድልድይ ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል ተባለ
በአቃቂ በበግ ተራ በኩል ያለው የመኪና መተላለፊያ ድልድይ ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጪ ሆኗል ተባለ፡፡የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥዑማይ ወልደገብርኤል ለሸገር ሲናገሩ በአቃቂ ትንሹ ድልድይ ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ በመዘጋቱ ሚኒባስ ታክሲዎችና በስፍራው ያሉ ፋብሪካዎች ሰርቪሶች መተላለፊያ አጥተው ስፍራው መጨናነቅ ገጥሞታል ብለዋል፡፡
በተሰበረው ድልድይ አቅራቢያ ተለዋጭ ድልድይ ለመሥራት የሚመች አይደለም ያሉት አቶ ጥዑማይ ከቶታል በኩል የሚመጡ መኪኖች በኪዳነ-ምህረት ቤተ-ክርስቲያን አድርገው ወደ ገላን በተቃራኒው የሚመጡ ደግሞ የቱሉ ዲምቱ ቀለበት መንገድን በተለዋጭነት ይጠቀሙ ብለዋል፡፡እነዚህ ተለዋጭ መንገዶች ረጅም ቢሆኑም የተሰበረው ድልድይ እስኪጠገን ብቸኛው አማራጭ ይኸው ነው ተብሏል፡፡
አሮጌውና ትልቁ የአቃቂ ድልድይም መሰነጣጠቅ እየገጠመው ስለሆነ ከ3 ቶን በላይ ክብደት ያላቸው መኪኖች እንዳይጓጓዙበት የአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ማስጠንቀቁን ነግረናችሁ ነበር፡፡
ወንድሙ ሀይሉ

0 Comments
0 Shares