የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ

የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ…የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ከ3 ትውልድ በላይ በማሣለፍ እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት ሀገሪቱን ለጠቀሙ ወገኖች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲያገኙ በተወሰነው መሠረት ቤተ-እሥራኤላውያን፣ የራስ-ተፈሪያን እምነት ተከታዮችና ልዩ ልዩ ግለሰቦች ይህን መብት እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡

የውጭ ሀገር ዜጎቹ የኢትዮጵያን ፓስፓርት ሲያገኙ ያለምንም የመኖሪያ ፈቃድና ቪዛ እንደልባቸው መመላለስ ይችላሉ፡፡በመዋዕለ-ነዋይ በኩልም ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለዋል፡፡ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት ወቅታዊ መግለጫቸው ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ትናንት ለሁለተኛ ጊዜ ያራዘመው የምህረት አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው ከቅድመ ሁኔታ ጋር እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምህረት ጊዜውን ተጠቅመው ወደ ሀገር ቤት በአፋጣኝ ካልተመለሱ የተሰጠው የምህረት ጊዜ ሊታጠፍ ይችላል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ፓስፓርት እንዲያገኙ የፈቀደላቸው ወገኖችን በተመለከተ ዝርዝር የአፈፃፀም ደንብ አዘጋጅቷል መባሉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡በሳውዲ አረቢያ የሚገኖሩና ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ አዲስ አበባ ሲደርሱ ከቀይ-መስቀል፣ ከፖሊስ፣ ከአይ.ኦ.ኤም እንደዚሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራውን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን አባላትን ቦሌ አየር ማረፊያ በመውሰድ አሳይቷቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ የኢትዮጵያ መንግሥት በልዩ ልዩ አስተዋፅኦ አገልግለውኛል ላላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲሰጥ መወሰኑ ተሠማ…የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መለስ አለም ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ከ3 ትውልድ በላይ በማሣለፍ እንዲሁም በልዩ ልዩ አገልግሎት ሀገሪቱን ለጠቀሙ ወገኖች የትውልደ ኢትዮጵያ ፓስፓርት እንዲያገኙ በተወሰነው መሠረት ቤተ-እሥራኤላውያን፣ የራስ-ተፈሪያን እምነት ተከታዮችና ልዩ ልዩ ግለሰቦች ይህን መብት እንዲያገኙ ተወስኗል፡፡ የውጭ ሀገር ዜጎቹ የኢትዮጵያን ፓስፓርት ሲያገኙ ያለምንም የመኖሪያ ፈቃድና ቪዛ እንደልባቸው መመላለስ ይችላሉ፡፡በመዋዕለ-ነዋይ በኩልም ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደርጋታል ብለዋል፡፡ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት ወቅታዊ መግለጫቸው ላይ የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ትናንት ለሁለተኛ ጊዜ ያራዘመው የምህረት አዋጅ ተግባራዊ የሚሆነው ከቅድመ ሁኔታ ጋር እንደሆነ አስታውሰዋል፡፡ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የምህረት ጊዜውን ተጠቅመው ወደ ሀገር ቤት በአፋጣኝ ካልተመለሱ የተሰጠው የምህረት ጊዜ ሊታጠፍ ይችላል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን ፓስፓርት እንዲያገኙ የፈቀደላቸው ወገኖችን በተመለከተ ዝርዝር የአፈፃፀም ደንብ አዘጋጅቷል መባሉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሰምተናል፡፡በሳውዲ አረቢያ የሚገኖሩና ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የተደረጉ ኢትዮጵያውያን በተመለከተ አዲስ አበባ ሲደርሱ ከቀይ-መስቀል፣ ከፖሊስ፣ ከአይ.ኦ.ኤም እንደዚሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራውን የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን አባላትን ቦሌ አየር ማረፊያ በመውሰድ አሳይቷቸዋል፡፡
0 Comments 0 Shares