የማንችስተር ደርቢ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ

በሜዳው ኢትሃድ ተቀናቃኙን ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናገው የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ ቢኖረውም ጎል ማስቆጠር ሳይችል ወጥቷል።

በርካታ ተጫዋቾቹን በጉዳት ያጣው ማንችስተር ዩናይትድ ተከላክሎ በመጫዎት አንድ ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።

የዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ የ24 ጨዋታ ያለመሸነፍ ጉዞቸውን አስጠብቀው በመውጣታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

በጨዋታው የዩናይትድ ማሩዋን ፌላኒን በሁለት ቢጫ ካርድ አጥቶታል።።ከጉዳት ወደ ሜዳ ተቀይሮ የገባው ገብርኤል ጀሱስ በግንባሩ ያስቆጠርው ጎል ከጨዋታ ውጭ በመባልም ተሽሯል።

በፕርሚየር ሊጉ ሁለቱም ቡድኖች እኩል 5 ጨዋታ ቀሪ ጨዋታ አላቸው፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ33 ጨዋታ 65 ነጥብ በመያዝ 4ኛ ማንችስተር ዩናይትድ 33 ጨዋታ 64 ነጥብ 5 ደረጃ ፣ አርሰናል ደግሞ በ60 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
የማንችስተር ደርቢ ያለ ግብ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ በሜዳው ኢትሃድ ተቀናቃኙን ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናገው የፔፕ ጋርዲዮላው ማንችስተር ሲቲ ሙሉ የጨዋታ ብልጫ ቢኖረውም ጎል ማስቆጠር ሳይችል ወጥቷል። በርካታ ተጫዋቾቹን በጉዳት ያጣው ማንችስተር ዩናይትድ ተከላክሎ በመጫዎት አንድ ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል። የዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኖ የ24 ጨዋታ ያለመሸነፍ ጉዞቸውን አስጠብቀው በመውጣታቸው ደስተኛ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ በጨዋታው የዩናይትድ ማሩዋን ፌላኒን በሁለት ቢጫ ካርድ አጥቶታል።።ከጉዳት ወደ ሜዳ ተቀይሮ የገባው ገብርኤል ጀሱስ በግንባሩ ያስቆጠርው ጎል ከጨዋታ ውጭ በመባልም ተሽሯል። በፕርሚየር ሊጉ ሁለቱም ቡድኖች እኩል 5 ጨዋታ ቀሪ ጨዋታ አላቸው፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ33 ጨዋታ 65 ነጥብ በመያዝ 4ኛ ማንችስተር ዩናይትድ 33 ጨዋታ 64 ነጥብ 5 ደረጃ ፣ አርሰናል ደግሞ በ60 ነጥብ 6ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡
Like
1
0 Comments 0 Shares