አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ወንዶች ጥሎ ማለፍ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ተደርገዋል።
ለትናንት ፕሮግራም ተይዞላቸው የነበሩት አዲስ አበባ ከተማ ከጅማ አባ ቡና እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወላይታ ዲቻ ጨዋታዎች ናቸው ዛሬ የተደረጉት።
በሰበታ ስታዲየም ረፋድ ላይ እና ምሳ ሰዓት በተደረጉት ሁለት ጨዋታዎች፥ ጅማ አባ ቡና እና ወላይታ ዲቻ ግማሽ ፍጻሜ መግባታቸውን አረጋግጠዋል።
ረፋድ ላይ በተደረገው ጨዋታ አዲስ አበባ ከተማ ከጅማ አባ ቡና ተጫውተዋል።
መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ምንም ጎል ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ጅማ አባ ቡና 5 ለ 4 በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።
ምሳ ሰዓት ላይ በተደረገው ሌላ ጨዋታ ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወላይታ ዲቻ ተገናኝተዋል።
ጨዋታው በተመሳሳይ መልኩ ጎል ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ነበር የተጠናቀቀው።
በመለያ ምትም ወላይታ ዲቻ 4 ለ 3 በማሸነፍ አራተኛው የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
መከላከያ እና ወልዲያ ከተማ ከዚህ ቀደም ግማሽ ፍጻሜውን መቀላቀል የቻሉ ቡድኖች ናቸው።
ግማሽ ፍጻሜ ለመግባት ከተደረጉ አራት ጨዋታዎች መካከል ሶስቱ በመለያ ምት ተጠናቀዋል።
ወልዲያ ከተማ ፋሲል ከነማን 2 ለ 0 ያሸነፈበት ጨዋታ ብቸኛው በመደበኛ ዘጠና ደቂቃ የተጠናቀቀ ጨዋታ ነው።

0 Comments
0 Shares