አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩስያ አቻቸው ጋር በቀጣዩ ሳምንት በጀርመን እንደሚወያዩ ዋይት ሀውስ አረጋገጠ።
የአሜሪካ ብሄራዊ የደህንነት አማካሪ ሀርበርት ሬሞንድ ማክማስተር እንደተናገሩት፥ ሁለቱ መሪዎች ከቡድን 20 አባል ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ነው በሀምቡርግ የሚመክሩት።
የህብረቱ አባል ሀገራት ጉባኤ ከሰኔ 30 እስከ ሀምሌ 1 2009 ይደረጋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ከዚህ ቀደም ግልፅ እንዳደረጉት ሩስያ ከአሜሪካም ሆነ ከምዕራቡ አለም ጋር ያላት ግንኙነት እንዲሻሻል ትፈልጋለች ነው ያሉት አማካሪው።
በመሪዎቹ ውይይት ሩስያ በ2016ቱ የአሜሪካ ምርጫ ጣልቃ ገብተሻል በሚል የቀረበባትን ወቀሳ አስመልክቶ ሊመክሩ እንደሚችሉ ግን ያሉት ነገር የለም።
የትራምፕ አስተዳደር ከሩስያ እና የተወሰኑ አማካሪዎቻቸው ከሞስኮ ጋር ያላቸው ግንኙነት በ2016ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል በሚል መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል።
በምርጫው የሞስኮ ተሳትፎ ስለመኖሩም የማጣራት ስራው ቀጥሏል።
ትራምፕ በተለያዩ አጋጣሚዎች አሜሪካ ከሩስያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ እንደምትሰራ መግለፃቸው ይታወሳል።
ፑቲን በበኩላቸው የሞስኮ እና ዋሽንግተን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም እንደሚያስጠብቅ መናገራቸው አይዘነጋም።
አሜሪካ እና ሩስያ በሶሪያ እና ዩክሬን ግጭት ጨምሮ በሌሎች ሀገራት ዙሪያ በሚከተሏቸው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዙሪያ ሲወዛገቡ ይታያል።
ዋሽንግተን እና አጋሮቿ የምስራቃዊ ዩክሬን አፍቃሪ ሩስያ ሀይሎችን ደግፋለች በሚል በሞስኮ ላይ ሰፊ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሏ ይታወቃል።
ምንጭ፦ ፕሬስ ቲቪ

0 Comments
0 Shares