አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ቅንጡ ህይወታቸውን ለመግለፅ እና የብዙዎችን ቀልብ ለመሳብ በስፖርት መኪና ወይም በሊሞዚን ከቦታ ቦታ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡

ከዚህ በተቃራኒው ቻይናዊው የሶስት ዓመት ህጻን ወደ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ሁልጊዜ የሚሄደው በበሬ፣ በፈረስ ወይም በአህያ ጀርባ ላይ ሆኖ ነው፡፡

አባቱም በእግራቸው እየሄዱ ልጃቸው የሚጓዝበትን እንስሳ እየጎተቱና እየመሩ የሚያደርሱት ሲሆን፥ ይህ ዘወትራዊ የመጓጓዣ መንገድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎችን እያነጋገረ ነው፡፡

በደቡባዊ ቻይና የሲቹዋን ግዛት ዋና ከተማ ቼንግዱ የሚኖሩት አባት እና ልጅ ከቤታቸው 3 ኪሎሜትር ወደሚርቀው ትምህርት ቤት የሚጓዙት በእንዲህ መልኩ ነው፡፡

በሬ፣ አህያ እና ትንሽ ፈረስ በየእለቱ እየተቀያየሩ ህጻኑን ወደ ትምህርት ቤት ይወስዳሉ፡፡

ሶስቱም እንስሳት የቻይና ስልጣኔ አድናቂ እና አስቀጣይ በሆኑት የህጻኑ አባት ሊ ሊ፥ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡

ሊ ሊ ጥንታዊው "የሀገራችን ስልጣኔ እና ባህል የዕለት ተዕለት ህይወታችን አንድ አካል መሆን አለበት" የሚል አቋም አላቸው፡፡

"ልጄ በበሬው ወይም በአህያዋ ወደ ትምህርት ቤት ሲጓጓዝ ለህጻናት ያለው ፍቅር ይጨምርለታል” ነው ያሉት ሊ፡፡

ህፃኑ በፈረስ፣ በሬ ወይም አህያ ጀርባ ላይ ሆኖ በየዕለቱ መጓዙ አባት ለልጃቸው ስለቻይና ስልጣኔ፣ ስለ ወቅታዊ ነገሮች እና የዛፍ ተከላ እንዲያስተምሩት እድልን ፈጥሯል፡፡

ሆኖም እናት የልጃቸውን በእንስሳቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ትምህርት ቤት መጓዝን ወድቆ ይጎዳብኛል በሚል አልወደዱትም፡፡

ሊ ሊ ደግሞ ሁኔታውን በሌላ መንገድ ነው የሚገልጹት፤ “በሬ እና አህያ የተረጋጉ የመጓጓዣ እንስሳት በመሆናቸው በልጄ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስም” በማለት፡፡

ህጻናት በአሁኑ ጊዜ ጥንታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን እየረሱ የማንነት ቀውስ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ዘመናዊውንም ሆነ ባህላዊውን ህይወት እያሳወቁ ማሳደግ ይገባል ነው የሚሉት ሊ፡፡

ቻይና በመንግስት ደረጃ ፈረስን፣ አህያን፣ በሬን ወይም ሌሎች እንስሳትን በመጓጓዣነት መጠቀምን ትፈቅዳለች።

ሆኖም በእንስሳት የሚጓጓዙ ሰዎች ተሸከርካሪ በማይሄድባቸው መንገዶች ሊጠቀሙ እንደሚገባ ትመክራለች፡፡

አንዳንድ ጊዜ በእንስሳት የሚጓዙ ሰዎች በተሸከርካሪ መንገድ ላይ በመግባት የትራፊክ ፍሰቱ ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ እና የትራፊክ ፖሊሶችም በሌላ መንገድ እንዲጠቀሙ እንደሚያደርጓቸው ይነገራል፡፡

በቻይና ማህበራዊ የትስስር ገጽ በሆነው ወይቦ፥ “የህጻኑን በበሬ ጀርባ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ እና በቻይና ስልጣኔ መካከል ግንኙነት አለን?” የሚል ጥያቄ ያነሱ አሉ።

ሌሎቹ ደግሞ የህጻኑ አባት ልጁን ስለ ጥንታዊ የቻይና ስልጣኔ ለማስተማር የተጠቀሙበትን መንገድ አድንቀዋል።

ምንጭ፡- http://en.people.cn/
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትላልቅ ከተሞች የሚኖሩ ሰዎች ቅንጡ ህይወታቸውን ለመግለፅ እና የብዙዎችን ቀልብ ለመሳብ በስፖርት መኪና ወይም በሊሞዚን ከቦታ ቦታ ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ቻይናዊው የሶስት ዓመት ህጻን ወደ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ሁልጊዜ የሚሄደው በበሬ፣ በፈረስ ወይም በአህያ ጀርባ ላይ ሆኖ ነው፡፡ አባቱም በእግራቸው እየሄዱ ልጃቸው የሚጓዝበትን እንስሳ እየጎተቱና እየመሩ የሚያደርሱት ሲሆን፥ ይህ ዘወትራዊ የመጓጓዣ መንገድ የቻይና ማህበራዊ ሚዲያዎችን እያነጋገረ ነው፡፡ በደቡባዊ ቻይና የሲቹዋን ግዛት ዋና ከተማ ቼንግዱ የሚኖሩት አባት እና ልጅ ከቤታቸው 3 ኪሎሜትር ወደሚርቀው ትምህርት ቤት የሚጓዙት በእንዲህ መልኩ ነው፡፡ በሬ፣ አህያ እና ትንሽ ፈረስ በየእለቱ እየተቀያየሩ ህጻኑን ወደ ትምህርት ቤት ይወስዳሉ፡፡ ሶስቱም እንስሳት የቻይና ስልጣኔ አድናቂ እና አስቀጣይ በሆኑት የህጻኑ አባት ሊ ሊ፥ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡ ሊ ሊ ጥንታዊው "የሀገራችን ስልጣኔ እና ባህል የዕለት ተዕለት ህይወታችን አንድ አካል መሆን አለበት" የሚል አቋም አላቸው፡፡ "ልጄ በበሬው ወይም በአህያዋ ወደ ትምህርት ቤት ሲጓጓዝ ለህጻናት ያለው ፍቅር ይጨምርለታል” ነው ያሉት ሊ፡፡ ህፃኑ በፈረስ፣ በሬ ወይም አህያ ጀርባ ላይ ሆኖ በየዕለቱ መጓዙ አባት ለልጃቸው ስለቻይና ስልጣኔ፣ ስለ ወቅታዊ ነገሮች እና የዛፍ ተከላ እንዲያስተምሩት እድልን ፈጥሯል፡፡ ሆኖም እናት የልጃቸውን በእንስሳቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ትምህርት ቤት መጓዝን ወድቆ ይጎዳብኛል በሚል አልወደዱትም፡፡ ሊ ሊ ደግሞ ሁኔታውን በሌላ መንገድ ነው የሚገልጹት፤ “በሬ እና አህያ የተረጋጉ የመጓጓዣ እንስሳት በመሆናቸው በልጄ ላይ ምንም ዓይነት አደጋ አይደርስም” በማለት፡፡ ህጻናት በአሁኑ ጊዜ ጥንታዊ እና ባህላዊ ትውፊቶችን እየረሱ የማንነት ቀውስ ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ዘመናዊውንም ሆነ ባህላዊውን ህይወት እያሳወቁ ማሳደግ ይገባል ነው የሚሉት ሊ፡፡ ቻይና በመንግስት ደረጃ ፈረስን፣ አህያን፣ በሬን ወይም ሌሎች እንስሳትን በመጓጓዣነት መጠቀምን ትፈቅዳለች። ሆኖም በእንስሳት የሚጓጓዙ ሰዎች ተሸከርካሪ በማይሄድባቸው መንገዶች ሊጠቀሙ እንደሚገባ ትመክራለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ በእንስሳት የሚጓዙ ሰዎች በተሸከርካሪ መንገድ ላይ በመግባት የትራፊክ ፍሰቱ ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ እና የትራፊክ ፖሊሶችም በሌላ መንገድ እንዲጠቀሙ እንደሚያደርጓቸው ይነገራል፡፡ በቻይና ማህበራዊ የትስስር ገጽ በሆነው ወይቦ፥ “የህጻኑን በበሬ ጀርባ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ እና በቻይና ስልጣኔ መካከል ግንኙነት አለን?” የሚል ጥያቄ ያነሱ አሉ። ሌሎቹ ደግሞ የህጻኑ አባት ልጁን ስለ ጥንታዊ የቻይና ስልጣኔ ለማስተማር የተጠቀሙበትን መንገድ አድንቀዋል። ምንጭ፡- http://en.people.cn/
WWW.FANABC.COM
FBC - አሜሪካዊው አዛውንት በስህተት ልጃቸው ያልሆነን ሰው ቀብረዋል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የልጃቸውን እርም ያወጡት አሜሪካዊው አዛውንት ከልጃቸው ጋር በድጋሚ ተገናኝተዋል። በወሩ መጀመሪያ አካባቢ እርሳቸው በሚኖሩበትና ፋውንቴን ቫሊ በተባለው አካባቢ አንድ ሰው ሞቶ ይገኛል። የ...
0 Comments 0 Shares