ፍርድ ቤቱ ቅቤን ከባእድ ነገር ጋር ደባልቀው ሸጠዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ቀጣ – ጎባ ሚያዝያ 19/2009 የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅቤን ከባእድ ነገር ጋር ደባልቀው ሸጠዋል ባላቸው ሁለት ተከሳሾች ላይ የአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ወሰነ፡፡

ፍርድ ቤቱ አበበች መዘንጊያና ፀሃይ ተሾመ በተባሉ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው ትናንት በዋለው ችሎት ነው።

ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን የወሰነው ተከሳሾቹ ሰኔ 25 ቀን 2008 በባሌ ጎባ ከተማ 04 ቀበሌና በሌሎች አካባቢዎች በመዘዋወር ከባእድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ቅቤ ለግለሰቦች መሸጣቸው በማስረጃ በመረጋገጡ መሆኑን የፍርድ ቤቱ ዳኛ ደረጃ መኮንን ገልጸዋል።

ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለው ቅቤ በኤግዚብትነት ተይዞ ናሙናው ለኢተዮዽያ የጥራት ደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን የተላከ ሲሆን ምንም አይነት የንጹህ ቅቤ በህሪ እንደሌለው በተካሄደው ምርመራ መረጋገጡን ተናግረዋል።

ተከሳሾቹ ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ቢከራከሩም የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔውን ሊያስተላለፍ ችሏል።

ተከሳሾቹ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የክስ ቻርጅ እንደሌለባቸውና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው እንደ ፍርድ ማቀለያ ተይዞ እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ፅኑ እስራትና በ2 ሺህ 500 ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኖባቸዋል – ENA
ፍርድ ቤቱ ቅቤን ከባእድ ነገር ጋር ደባልቀው ሸጠዋል ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በእስራትና በገንዘብ ቀጣ – ጎባ ሚያዝያ 19/2009 የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅቤን ከባእድ ነገር ጋር ደባልቀው ሸጠዋል ባላቸው ሁለት ተከሳሾች ላይ የአምስት ዓመት ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ወሰነ፡፡ ፍርድ ቤቱ አበበች መዘንጊያና ፀሃይ ተሾመ በተባሉ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው ትናንት በዋለው ችሎት ነው። ፍርድ ቤቱ ቅጣቱን የወሰነው ተከሳሾቹ ሰኔ 25 ቀን 2008 በባሌ ጎባ ከተማ 04 ቀበሌና በሌሎች አካባቢዎች በመዘዋወር ከባእድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ቅቤ ለግለሰቦች መሸጣቸው በማስረጃ በመረጋገጡ መሆኑን የፍርድ ቤቱ ዳኛ ደረጃ መኮንን ገልጸዋል። ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለው ቅቤ በኤግዚብትነት ተይዞ ናሙናው ለኢተዮዽያ የጥራት ደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን የተላከ ሲሆን ምንም አይነት የንጹህ ቅቤ በህሪ እንደሌለው በተካሄደው ምርመራ መረጋገጡን ተናግረዋል። ተከሳሾቹ ድርጊቱን አልፈጸምንም ብለው ቢከራከሩም የቀረበባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የባሌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔውን ሊያስተላለፍ ችሏል። ተከሳሾቹ ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የክስ ቻርጅ እንደሌለባቸውና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው እንደ ፍርድ ማቀለያ ተይዞ እያንዳንዳቸው በአምስት ዓመት ፅኑ እስራትና በ2 ሺህ 500 ብር እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ወስኖባቸዋል – ENA
Like
1
0 Comments 0 Shares