አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፉ በተለይ ለአልሚ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ 277 ሺህ ህጻናት እና ሴቶች አስቸኳይ እርዳታዎችን ለመስጠት ያገዛል ተብሏል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ላ ይፋን በእርዳታ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት፥ ቻይና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር በመሆኗ የተቻላትን ድጋፍ እያደረገች ነው፡፡
“በማደግ ላይ የምንገኝ ሀገር ብንሆንም በአለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ ማደረግ አለብን” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን በተመለከተ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት አምባሳደሩ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቀነስ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጆን አይሊፍ በበኩላቸው፥ ቻይና በአንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ኢትዮጵውያን እያደረገች ያለችውን አስተዋጽኦ አድንቀው፥ በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ከ50 አመታት ወዲህ የከፋ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ አቅም ደርቁን ለመቋቋም እና ለዜጎቹ በወቅቱ አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ መሆኑን ያደነቁት ዳይሬክተሩ፥ አለም አቀፉ ማህበረሰብም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
በዚህ ወቅት ቻይና ያደረገችው እርዳታንም በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት የአልሚ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ቁጥርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን የአለም ምግብ ፕሮገራም በደረ ገጹ የጠቀሰ ሲሆን፥ 40 በመቶ ከሚሆኑ ህጻናት ውስጥ 9 በመቶው የመቀጨር ችግር ያሉባቸው በመሆኑ ችግሩን ለመቀነስ ብርቱ ጥረት እንደሚጠይቅ ጠቁሟል፡፡
ምንጭ ፦http://www.vanguardngr.com

0 Comments
0 Shares