አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ።
የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል።
በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል።
ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል።
ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል።
በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል።
ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ።
ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት።
ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል።
የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።
በስላባት ማናዬ

0 Comments
0 Shares