አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚገኙ ግለሰቦች ተናገሩ።
አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት፥ ህገወጥ ዓሳ አስጋሪዎቹ ባልተገባ ሁኔታ ዓሳዎችን እንቁላል ሳይጥሉ ማስገራቸው የሀይቁ የዓሳ ሃብት እንዲቀንስ አድርጎታል።
የማጥመድ ስራውም ማንኛውንም አሳ ለማጥመድ ከውጭ ሀገር በመጣ ማጥመጃ እያከናወኑ መሆኑም ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል።
ይህ ደግሞ ትናንሽ አሳዎችን ከሀይቁ በማውጣት ተተኪ እንዳይኖር ያደርገዋል ነው የተባለው።
የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሀይቁ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ እና ህገወጥ አስጋሪዎች፥ የሚያሰግሩበትን መንገድ እንዲያስተካክሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ዓሳ የሚያሰግሩበት ማስገሪያ በተቀመጠለት ደረጃ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ ሲሆን፥ እርምጃ ለመውሰድም ታቅዷል።
ሀይቁ የኦሮሚያ ክፍል አዋሳኝ በምዕራብ አርሲ ዞን ከ300 በላይ ወጣቶች በማህበር የስራ እድል ተፈጥሮላቸው፥ በቢሻን ጉራቻ ሐይቅ ዳርቻ ተሰማርተው እየሰሩ ሲሆን፥ በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገሩም በእነሱ በኩልም እየተከናወነ ነው።
የዞኑ የእንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ ሃላፊ ዶክተር አብዱላሂ ቤካ፥ የወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገር ችግር አምነው፥ ከፌደራልና ከደቡብ ክልል የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል።

0 Comments
0 Shares