በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ

በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ፡፡ በ170 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመኪና ማቆሚያ ስፍራው ዘመናዊ ነው የተባለ ሲሆን 15 ፎቆች ላይ እንዲሁም በምድር ላይ መኪኖችን ያሳርፋል ተብሏል፡፡

የመኪና ማቆሚያው በፎቆቹ ላይ 90 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ሲሆን የምድሩ ደግሞ 50 መኪኖችን ማቆም እንደሚያስችል ወይዘሮ ታፈሱ አባይ በትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ለመኪና ማቆሚያዎቹ ሥፍራ ግንባታ በመንግሥት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውም ሰምተናል፡፡

የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የሙከራ ሥራ የጀመሩት የመገናኛ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥፍራው በምን ያህል ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ግን ተመን አልወጣለትም ተብሏል፡፡

የመኪና ማቆሚያ ሥፍራው ለ20 ዜጐች የሥራ እድል እንደፈጠረም ተነግሯል፡፡በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድና ወሎ ሰፈር አካባቢዎች ላይም የተጀመሩት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃሉ የተባለ ቢሆንም መዘግየት አላጋጠመም ወይ ብለን የጠየቅናቸው ወይዘሮ ታፈሱ የወሎ ሰፈሩና የአንዋር ወስጊዱ በቅርቡ ይጠናቀቃል አልዘገየም ያሉ ሲሆን በቸርችል ጐዳና የሚገነባው ደግሞ ከመሬት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ትንሽ ውዝግብ ተነስቶ ነበረ አሁን ችግሩ ስለተፈታ በቅርቡ ሥራው ይጀመራል ብለዋል፡፡

በከተማዋ 60 የተመረጡ ቦታዎች ላይም ሌሎች የመኪና ማቆሚያዎች ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምሕረት ስዩም
ሸገር
በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ በአዲስ አበባ እየተገነቡ ካሉት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች በመገናኛ ዘፍመሽ አካባቢ ያለው የመኪና ማቆሚያ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ ጀምሯል ተባለ፡፡ በ170 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው የመኪና ማቆሚያ ስፍራው ዘመናዊ ነው የተባለ ሲሆን 15 ፎቆች ላይ እንዲሁም በምድር ላይ መኪኖችን ያሳርፋል ተብሏል፡፡ የመኪና ማቆሚያው በፎቆቹ ላይ 90 ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚያስችል ሲሆን የምድሩ ደግሞ 50 መኪኖችን ማቆም እንደሚያስችል ወይዘሮ ታፈሱ አባይ በትራንስፖርት ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደት መሪ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ለመኪና ማቆሚያዎቹ ሥፍራ ግንባታ በመንግሥት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸውም ሰምተናል፡፡ የግንባታ ሥራቸው ተጠናቆ የሙከራ ሥራ የጀመሩት የመገናኛ አካባቢ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባሉ ተብሏል፡፡ዘመናዊ የፓርኪንግ ሥፍራው በምን ያህል ተመን አገልግሎት እንደሚሰጥ ግን ተመን አልወጣለትም ተብሏል፡፡ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራው ለ20 ዜጐች የሥራ እድል እንደፈጠረም ተነግሯል፡፡በአዲስ አበባ አንዋር መስጊድና ወሎ ሰፈር አካባቢዎች ላይም የተጀመሩት ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች ግንባታ በቅርቡ ይጠናቀቃሉ የተባለ ቢሆንም መዘግየት አላጋጠመም ወይ ብለን የጠየቅናቸው ወይዘሮ ታፈሱ የወሎ ሰፈሩና የአንዋር ወስጊዱ በቅርቡ ይጠናቀቃል አልዘገየም ያሉ ሲሆን በቸርችል ጐዳና የሚገነባው ደግሞ ከመሬት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ትንሽ ውዝግብ ተነስቶ ነበረ አሁን ችግሩ ስለተፈታ በቅርቡ ሥራው ይጀመራል ብለዋል፡፡ በከተማዋ 60 የተመረጡ ቦታዎች ላይም ሌሎች የመኪና ማቆሚያዎች ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ምሕረት ስዩም ሸገር
0 Comments 0 Shares