ጋቶች ፓኖም ለአንዚ ማካቻካላ ፈረመ
ኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ለሩስያው ክለብ አንዚ ማካቻካላ ለመጫወት ትናንት ተፈራረመ፡፡
የተጫዋቹ ወኪል ዴቪድ በሻ እንደገለፀው፥ ጋቶች ለሶስት ዓመት ለማካቻካላ ከተማው ክለብ ለመጫወት ተስማምቷል።
ጋቶች ከሳምንት በፊት ወደ ሩስያ አቅንቶ የሙከራ ጊዜ እያሳለፈ ይገኝ የነበረ ሲሆን የሙከራ ጊዜው የአንዚ ክለብ አሰልጣኞችን ያስደሰተ በመሆኑ ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅተዋል።
የክለቡ ፕሬዚደንት በፊፋ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሃገራቸው ሩስያ ከኒውዝላንድ ያደረገችውን የመክፈቻ ጨዋታ ለመታደም ወደ ሞስኮ አምርተው ስለነበር የጋቶች እና አንዚ ዝውውር ጉዳይ ዘግይቶ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጫዋቹ የአንዚ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል ነው ያለው ወኪሉ።
አንዚ ማካቻካላ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ስሎቬኒያ ያመራ ሲሆን የቪዛ ጉዳዮችን ጨርሶ አዲሱ ፈራሚ ጋቶችም በቅርቡ እንደሚቀላቀላቸው ይጠበቃል፡፡
ጋቶች በኢትዮጵያ ቆይታው ከታዳጊነቱ ጀምሮ ላሳደገው ኢትዮጵያ ቡና በመጫወት አሳልፏል፡፡
በዘንድሮው የውድድር ዓመትም ስምንት የሊግ ግቦችን ለቡና ማስቆጠር መቻሉን ሶከር ኢትዮጵያ ዋቢ አድርጎ ያደረሰን ፋና ብሮድካሲቲንግ ኮርፖሬት ነው፡፡
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2009
ጋቶች ፓኖም ለአንዚ ማካቻካላ ፈረመ ኢትዮጵያዊው አማካይ ጋቶች ፓኖም ለሩስያው ክለብ አንዚ ማካቻካላ ለመጫወት ትናንት ተፈራረመ፡፡ የተጫዋቹ ወኪል ዴቪድ በሻ እንደገለፀው፥ ጋቶች ለሶስት ዓመት ለማካቻካላ ከተማው ክለብ ለመጫወት ተስማምቷል። ጋቶች ከሳምንት በፊት ወደ ሩስያ አቅንቶ የሙከራ ጊዜ እያሳለፈ ይገኝ የነበረ ሲሆን የሙከራ ጊዜው የአንዚ ክለብ አሰልጣኞችን ያስደሰተ በመሆኑ ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅተዋል። የክለቡ ፕሬዚደንት በፊፋ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሃገራቸው ሩስያ ከኒውዝላንድ ያደረገችውን የመክፈቻ ጨዋታ ለመታደም ወደ ሞስኮ አምርተው ስለነበር የጋቶች እና አንዚ ዝውውር ጉዳይ ዘግይቶ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጫዋቹ የአንዚ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል ነው ያለው ወኪሉ። አንዚ ማካቻካላ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ ስሎቬኒያ ያመራ ሲሆን የቪዛ ጉዳዮችን ጨርሶ አዲሱ ፈራሚ ጋቶችም በቅርቡ እንደሚቀላቀላቸው ይጠበቃል፡፡ ጋቶች በኢትዮጵያ ቆይታው ከታዳጊነቱ ጀምሮ ላሳደገው ኢትዮጵያ ቡና በመጫወት አሳልፏል፡፡ በዘንድሮው የውድድር ዓመትም ስምንት የሊግ ግቦችን ለቡና ማስቆጠር መቻሉን ሶከር ኢትዮጵያ ዋቢ አድርጎ ያደረሰን ፋና ብሮድካሲቲንግ ኮርፖሬት ነው፡፡ አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2009
Like
1
1 Comments 0 Shares