የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀርጌሳ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ላይ የሚጠቀመውን የቦታ አገላለጽ እንዲያስተካክል ሶማሊያ መንግሥት ያቀረበው ጥያቄ “ተቀባይነት አግኝቶ ማስተካከያ መደረጉን” የአገሪቱ ትራንስፖርት እና ሲቪል አቬዬሽን ሚኒስቴር ለቢቢሲ ገለጸ። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ ገጽ ላይ እስከ ዛሬ ረፋድ ድረስ “ሀርጌሳ” ብቻ በሚል ተጠቅሶ የነበረው ወደ ከተማዋ የሚደረግ በረራ ከሰዓት በኋላ “ሀርጌሳ፣ ሶማሊያ” በሚል ተቀይሯል።

0 Comments
0 Shares