በረኪናው
(አሳዬ ደርቤ)
እንዴት ከረማችሁልኝ? ሰሞኑን ትንሽ ችግር ብጤ አጋጥሞኝ ከፌስቡክ ጠፍቼ ከረምኩ፡፡ ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡
ከወራት በፊት አንድ ጓደኛዬ በስልኬ ደውሎ ለጥብቅ ጉዳይ እንደሚፈልገኝ ስለነገረኝ ስከንፍ ወደ ተቃጠርነበት ቦታ አመራሁ፡፡ ስፍራው ስደርስ ጓደኛዬ ቀድሞኝ ደርሶ አገኘሁት፡፡ ሰውነቱን ስታዘበው አካሉ ከሞጎሳቆሉም በላይ ጺሙ አድጓል፡፡
‹‹ለምን ፈልገኸኝ ነው?›› አልኩት የጀበና ቡናዬን እየተጎነጨሁ፡፡
የያዘውን ጥራዝ ወረቀት አቀበለኝ፡፡ የጥራዙ ሽፋን ላይ ‹‹የፈሳሽ ሳሙና (በረኪና) አዘገጃጀት›› የሚል ጽሁፍ በትልቁ ሰፍሮበታል፡፡
‹‹ስለ በረኪና አዘገጃጀት ማወቅ ምን ያደርግልኛል?›› አልኩት፡፡
‹‹ከተወሰኑ ጓደኞቼ ጋር ተደራጅቼ በረኪና ማምረት ልጀምር ነው!›› አለኝ፡፡
‹‹አምርታችሁ ምን ልታደርጉት?›› አልኩት ‘ልንጠጣው’ የሚል መልስ እየጠበኩኝ፡፡
‹‹ልንሸጠው!›› በማለት መለሰልኝ፡፡
‹‹ታዲያ ከኔ ምንድን ነው የምትፈልጉት?››
‹‹አብረን እንድንሰራ ነዋ! ፈሳሽ ሳሙና (በረኪና) ለማዘጋጀት የሚስፈልጉ ኬሚካሎችን ለይተን አውቀናቸዋል፡፡ አሁን የሚቀረን ነገር ጥሬ እቃዎቹን አስመጥተን በፋብሪካ እያመረቱ መሸጥ ብቻ ነው፡፡ ይሄን ለማድረግ ደግሞ ትንሽ የካፒታል እጥረት ስላጋጠመን አንድ ተጨማሪ ሰው ማስገባት ግደታ ሆኖብናል! ስለዚህ የኛን ያህል ብር ማዋጣት ከቻልክ አብረን ተጠቃሚ መሆን እንችላለን›› እያለ ማብራራቱን ቀጠለ፡፡
የተሰጠኝ ስብከት ከልጁ ኬሚካል ኢንጅነርነት ጋር ተዳምሮ አፍታም ሳልቆይ ወደ ህልም ውስጥ መግባት ጀመርኩኝ፡፡
.
በቅዠቴ መሃከል ይሄን ስብሰባ የሚበዛበትን ስራዬን ስለቀው ይታየኛል፡፡
በቅዠቴ መሃከል ሙሉአለም በእኛ በረኪና ጋቢዋን ስታቸፈችፍ፣ ሰራዊት ፍቅሬ ‹‹የISO ሁለት ሽ ስምንት ማረጋገጫ ያለው›› እያለ ጋቢውን ጠምዝዞ ሲያሰጣ በቴሌቪዥን ይታየኛል፡፡
በቅዠቴ መሃከል የኛን ብራንድ የተነቀሰች መኪና በረኪናችንን ጭና እንደ አምቡላንስ እየጮኸች ጓዳናውን ስትራወጥበት ይታየኛል፡፡
.
በማግስቱ የሚጠበቅብኝን ገንዘብ እቦታው ድረስ ወስጀ አስረከብኩት፡፡
በረኪና ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች እና ጥሬ እቃዎች ከየአገሩ እየተፈለጉ ተገዙ፡፡ ኬሚካል ኢንጅነሩ ገዋን ለብሶ፣ ጓንቱን አጥልቆ፣ መነጽሩን ሰክቶ ውሎና አዳሩን ላብራቶሪ ውስጥ አደረገ፡፡ ሲጃራ ሊያጨስና ምግብ ሊቀማምስ ከላብራቶሪ ሲወጣ እንኳን በአንድ እጁ እስኪብርቶ ጨብጦ ፎርሙላ በመደርደርና ፎርሙላ በመናድ ይጠመዳል፡፡
እዚህ ላይ ለሀገራችን ብዙ ምርምሮችን ያደረገው የበእውቱ ስዩም አያት ትዝ አለኝ፡፡ በእውቄ ይሄ ተማራማሪ አያቱ ከአንስታይን ጋር የሚጋራቸውን ባህሪዎች ሲዘረዝር እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹አንስታይን በምርምር ተጠምዶ ሲውል ምሳ መብላቱን ይረሳ ነበር፡፡ የኔም አያት በምርምር ሲጠመድ የበላውን ምሳ እየረሳ ሁለተኛ አምጡ ማለት ጀመረ!›› በማለት የተናገራት ስላቅ ታወሰችኝ፡፡
የእኔው ተመራማሪ ደግሞ በጀመረው ሂሳብ ላይ ከመመሰጡ የተነሳ የለኮሰው ሲጋራ ነዶ አልቆ፣ ጣቱን ሲያቃጥለው እንኳን አይሰማውም ነበር፡፡ እኛ ስለ በረኪናው እንጂ ስለ ፎርሙላው ሃሳቡ የሌለን ጓደኞቹ ‹‹ዩራኒየም ከማብላላት በረኪና ማብላላት በጣም እውቀትን ይጠይቃል›› የሚል መደምደሚ ላይ ደረስን፡፡
.
የተጠመቀው በረኪና የላብራቶሪ ሂደቱም ጨርሶ የሚሞከርበት ቀን ደረሰ፡፡ ፈሳሽ ሳሙናው በጠርሙስ ውስጥ ሲታይ መልኩም ሆነ ውፍረቱ ነጭ ወለላ ማር ይመስላል፡፡ ውሃ የያዘ ሳፋ ላይ ጠብታ በረኪና ተጨመረ፡፡ ወጥ እና ላብ ያቆሸሸው የተመራማሪያችን ገዋን በዚህ ታምረኛ ሳሙና ሊታጠብ ወደ ሳፋው ውስጥ ገባ፡፡
ልብስ አጣቢዋ (ላብ ቴክኒሽያኗ) በረኪናውን እንድኳርፍ ለማድረግ በጉራጌኛ ውዝዋዜ መዳፎቿን አሾረቻቸው፡፡ ግንባሯ ላይ ላቧ እስኪፈልቅ ድረስ ብትታገልም ወፍ እና መኳረፍ የሚባል ነገር ሳይታይ ቀረ፡፡
‹‹እስኪ በረኪናውን በደንብ አድርግበት›› አለው ከባለሀብቶቹ መሃከል አንዱ፡፡
የውሃው ቀለም እስኪለወጥ ዝርግፍ አድርጎ ጨመረበት፡፡
የማይኳርፍ በረኪና እና ያኮረፉ ፊቷች ላብራቶሪው ውስጥ ነገሱ፡፡ ሳፋው ውስጥ ሊታጠብ የገባው ገዋን የመቆሸሽ ሁኔታ ተስተዋለበት፡፡ ገዋኑን ለማንጻት የእኛን በረኪና የሚያስለቅቅ ሌላ በረኪና አስፈለገ፡፡ አንዱ ሸሪካችን ‹‹እንዴት ያን ሁሉ ገንዘብ ጨፍጭፈን በበረኪና ፈንታ ቆሻሻ ልናመርት ቻልን?›› በማለት ገዋኑን አንስቶ ወረወረው፡፡
.
አሁን የተመራማሪነቱን ሚና እኔ ወስጃለሁ፡፡ ከላብራቶሪው እየሮጥኩኝ በመውጣት ሜሪንዳና ወተት ይዠ ተመለስኩ፡፡
‹‹ምን ልታደርግ ነው?›› አሉኝ፡፡
‹‹እዚህ ሀገር በበረኪና ከሚያጥበው ይልቅ በረኪና የሚጠጣው ይበዛል! ስለዚህ የእኛ በረኪና እጥበቱ አርኪ ባይሆንም መርዘኝነቱ የተሻለ ሊሆን ይችላል! ይሄን ደግሞ እኔ ልሞክረው ወስኛለሁ! እናም በረኪናውን ጠጥቼ የመዝለፍለፍ ሁኔታ ካስተዋላችሁብኝ ወተቱን፣ ምንም ለውጥ ካልተከሰተ ደግሞ ሜሪንዳውን እንድትግቱኝ!›› በማለት ተናዘዝኩኝ፡፡ (ጊዜው የእኔ ተስፋ የተሟጠጠበት እና የሜሪንዳ ስም የጠፋበት ስለነበር፣ በረኪናው ለልብስ እጠበትም፣ ለነፍስ ማጥፋትም የማይሆን ከሆነ ሜሪንዳውን ጠጥቼ ይችን ምድር ለመሰናበት ወስኛለሁ፡፡)
በረኪና የያዘውን ጠርሙስ አነሳሁና ‹‹ዥው›› አድርጌ ጠጣሁት፡፡
እራሴን እንዲያዞረኝ፣ ሆዴን እንድያጥወለውለኝ ጾለት አደረስኩኝ፡፡ ጉልበቴ ተዳክ፣ ዐይኔ ተስለምልሞ ማየት ፈለኩኝ፡፡
ከግሳት ውጭ ምንም የተከሰተ ነገር አልነበረም፡፡ ‹‹ከዚህ በላይ መኖር መዋጮ ለመጠየቅ ነው›› አልኩና ሚሪንዳውን በማንሳት ባንድ ትንፋሽ ጨለጥኩት፡፡
የተዳከመ መንፈሴ ሲነቃቃ፣ በንደት የተቃጠለ ጨጓራየ ሲቀዘቅዝ ተሰማኝ፡፡
የላብራቶሪውን ጠረጴዛ በቡጢ ስጠልዘው እንክትክቱ ወጣ፡፡
እንዴ!! ይሄን ሁሉ ሃይል ከየት አመጣሁት?
ምናልባት የነ ‹‹ገንዘቤ›› አሰልጣኝ ሻንጣው ውስጥ የተገኘበት አበረታች መድሃኒት ይሄ ይሆን እንዴ?
ይሄን ለመመለስ ተጨማሪ ጊዜ እና ተጨማሪ ምርምር ይጠይቃል፡፡
እስከዚያው ግን ሰላም እደሩልኝ!

0 Comments
0 Shares