በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከአባቱ ሞት በኋላ ወደ እንግሊዝ የተወሰደው ልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ፣ ቤተሰቡን እና አገሩን ድጋሚ የማየት ዕድል ሳይገጥመው ነበር ሕይወቱ እዚያው በለጋነት ዕድሜው ያለፈው። ሥርዓተ ቀብሩም የብሪታኒያ ነገሥታት ከሚያርፉበት ለንደን ከሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ተፈጽሟል። የልዑሉ ህልፈት በርካታ ትውልዶችን ያሳለፈ ቢሆንም ቤተሰቦቹ እና ኢትዮጵያውያን አጽም ወደ አገሩ እንዲመለስ ሲጠይቁ ቆይተዋል። በአሁኑ ወቅት የልዑል ዓለማየሁ ቤተሰቦች ንጉሥ ቻርልስ ሦስተኛ ጥያቄያቸውን እንደሚመልሱላቸው ተስፋ አድርገዋል። ቢቢሲ ጥያቄውን ለባኪንግሃም ቤተ መንግሥት አቅርቦ ምላሽ አግኝቷል።

0 Comments
0 Shares