ዜጎች ወደተለያዩ የአረብ ሀገራት ለቤት ሰራተኝነት በህጋዊ መንገድ እንዳይሄዱ መንግስት ጥሎት የቆየውን እገዳ እንዲያነሳ ጥያቄ ማቅረቡን የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡
ስራ ፈላጊዎችን በህጋዊ መንገድ ለመላክም ከ3 ሰራተኛ ተቀባይ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ለመፈራረም ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅቶ መጨረሱን ሰምተናል፡፡
ስምምነቶቹ የሚፈረሙት ከሊባኖስ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ከባህሬን ጋር ነው ተብሏል፡፡
ሚኒስትሩ አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ እንዳሉት የተሰናዳው የስምምነት ረቂቅ አስተያየት እንዲሰጥበት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተልኳል፡፡
ከሳውዲ አረቢያ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱ የሚታወስ ሲሆን ስምምነቱ በመንግስት እንዲፀድቅ የሚቀርብ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ከሊባኖስ ጋር በቅርቡ ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በቀድሞው የስራ ስምሪት አዋጅ መሰረት ፈቃድ ተሰጥቷቸው ሲሰሩ የቆዩ 21 ነባር ኤጀንሲዎች ፈቃዳቸው መሰረዙን ሚኒስትሩ ዛሬ የመስሪያ ቤታቸውን የ6 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርት ለሕዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ሲያቀርቡ ሰምተናል፡፡
በአዲሱ አዋጅ መሰረት በውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛን ለማግኘት ካመለከቱ 820 አዳዲስና 178 ነባር ኤጀንሲዎች መካከል መስፈርቱን አሟልተዋል ተብለው ፈቃድ የተሰጣቸው 6 ኤጀንሲዎች ብቻ ናቸው፡፡ ሰነዳቸው እየታየ ያሉም አሉ ተብሏል፡፡
አዲሱ የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅ ከፀደቀ 2 አመት ቢሞላውም ወደ አረብ ሀገራት ለስራ የሚሄዱ ሰራተኞች እገዳ እስካሁን አልተነሳም አሁን ግን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያገባደድን ነው ያሉት ሚኒስትሩ መንግስት እገዳውን እንዲያነሳ ጥያቄ አቅርበን መልስ እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
(ትዕግስት ዘሪሁን)