ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ ሜኔራሎች እነማን ናቸው?
(በዳንኤል አማረ @ኢትዮጤና) #EthioTena #Minerals
✔ባዮቲን!
ባዮቲን ነርቮችን፣ ቆዳን እና የምግብ መፈጨት ስርዓትን ያግዛል። ለአዋቂ ወንድ እና ለሴቶች 30 ማይክሮ ግራም በቀን ያስፈልገናል። ሩብ ኩባያ ለውዝ 88% የባዮቲን የቀን ፍላጐታችንን ያሟል።
✔ካልሲየም!
ካልሲየም ለአጥንት እና ጥርስ ጥንካሬ ጠቃሚ የመሰረት ድንጋይ ሜኔራል ነው። በተጨማሪም ጡንቻ እና ነርቭ ተግባራቸውን እንዲወጡ አስተዋጽዎ ያደርጋል። አዋቂ ወንዶችና ሴቶች 800 ሚ.ግ. ካልሲየም ያስፈልጋቸዋል። አንድ ኩባያ እርጐ 30% የካልሲየም የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል።
✔ክሎሪን!
ክሎሪን የነርቭ ስርዓታችንን በማገዝ እና የሴል ሜምብሬን አቋም ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል። ለወንዶች 550 ሚ.ግ. ለሴቶች 425 ሚ.ግ. ክሎሪን በቀን ያስፈልጋል።አስር እግር ያለው ባለቅርፊት አሳ 36% የቀን ክሎሪን ፍላጐታችንን ያቀርባል።
✔ክሮሚየም!
ክሮሚየም ፋትን፣ ፕሮቲን፣ እና ካርቦሃይድሬት ለመፍጨት ያገለግላል። 35 ማይክሮግራም በቀን ያስፈልገናል ሴቶች 25 ማይክሮ ግራም ያስፈልጋቸዋል። ግማሽ ኩባያ ብርኮሊ 11 ማይክሮ ግራም ክሮሚየም ይሰጠናል።
✔ኮፐር!
ኮፐር አጥንት እና የተለያየ የሰውነት ክፍላችን ተቀናጅተው እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል በተጨማሪም ሀይል/ጉልበት ይሰጣቸዋል። 700 በቀን ለወንድ እና ሴት ያስፈልጋቸዋል።
✔ፍሎራይድ!
ፍሎራይድ ጥርስ እንዳይጐዳ ይከላከላል ጤናማ የሆነ አጥንት ለመገንባት ይጠቅማል። ከ0.1-0.5 ሚ.ግ. ለህፃናት፣ 4 ሚ.ግ. ለአዋቂ ወንድ 3 ሚ.ግ. ለአዋቂ ሴቶች በቀን ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ከመጠጥ ውሃ የፍሎራይድ ፍላጐታችንን እናሟላለን።
✔ፎሌት!
ፎሌት የደም ሴሎቻችን እንዲመረቱ ለማድረግ ይጠቅማል በተለይ ለእርጉዝ ሴቶች ይጠቅማል። 300 ዮጂኤስ ለሴቶችን ወንዶች በቀን ያስፈልጋል። አንድ ኩባያ ምስር 90% የፎሌት ፍላጐታችንን ያሟላል።
✔አዮዲን!
አዮዲን ጤናማ የታይሮይድ ሆርሞን እንዲመረት ያደርጋል። 95 ዮጂኤስ በቀን ለወንድ እና ሴቶች ያስፈልጋል። ስካሎፕ 90% የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል።
✔ብረት(IRON)!
ብረት (Iron) ኦክስጂን ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ወስጥ እንዲሰራጭ ያደርጋል በተጨማሪም ሀይል/ጉልበት እንዲመረት ድጋፍ ያደርጋል። 6 ሚ.ግ. ለወንድ 8.1 ሚ.ግ. ለሴቶች በቀን ያስፈልጋል። አንድ ኩባያ ስፒናች (አረንጓዴ የሚበላ ቅጠል) 36% የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል።
✔ማንጋኒዝ!
ማንጋኒዝ ለቆዳ ጤንነት፣ ጐጂ አንቲኦክሲዳንት በመከላከል፣ ጤናማ የስኳር መጠን እንዲኖረን በማድረግ ይጠቅመናል። 2-5 ሚ.ግ. በቀን ለአዋቂዎች ያስፈልጋቸዋል። አንድ ኩባያ ቡናማ ሩዝ 88% የማንጋኒዝ ፍላጐታችንን ያሟላል።
✔ማግኒዚየም!
ማግኒዚየም ሰውነታችን ጉልበት/ሀይል እንዲያመነጭ ያደርጋል፣ የነርቭ ስርዓታችንን ያመጣጥናል፣ የሰውነት መቆጣትን ይቆጣጠራል፣ የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል። 350 ሚ.ግ. ለወንዶች 265 ሚ.ግ. ለሴቶች በቀን ያስፈልጋል። ሩብ ኩባያ የድባ ፍሬ 48% የማግኒዚየም የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል።
✔ኒያሲን!
ኒያሲን ጉልበት/ሀይል ለማምረት ጠቃሚ ነው ጐጂ አንቲኦክሲዳንቶችን በመከላከል በሽታ እንዳይከሰት ያደርጋል። 12 ሚ.ግ. ለወንድ 11 ሚ.ግ. ለሴቶች በቀን ያስፈልጋል። የዶሮ ስጋ 97% የቀን ፍጆታችንን ያበረክታል።
መልካም ጤንነት!!!
ለሰውነታችን የሚያስፈልጉ ሜኔራሎች እነማን ናቸው? (በዳንኤል አማረ @ኢትዮጤና) #EthioTena #Minerals ✔ባዮቲን! ባዮቲን ነርቮችን፣ ቆዳን እና የምግብ መፈጨት ስርዓትን ያግዛል። ለአዋቂ ወንድ እና ለሴቶች 30 ማይክሮ ግራም በቀን ያስፈልገናል። ሩብ ኩባያ ለውዝ 88% የባዮቲን የቀን ፍላጐታችንን ያሟል። ✔ካልሲየም! ካልሲየም ለአጥንት እና ጥርስ ጥንካሬ ጠቃሚ የመሰረት ድንጋይ ሜኔራል ነው። በተጨማሪም ጡንቻ እና ነርቭ ተግባራቸውን እንዲወጡ አስተዋጽዎ ያደርጋል። አዋቂ ወንዶችና ሴቶች 800 ሚ.ግ. ካልሲየም ያስፈልጋቸዋል። አንድ ኩባያ እርጐ 30% የካልሲየም የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል። ✔ክሎሪን! ክሎሪን የነርቭ ስርዓታችንን በማገዝ እና የሴል ሜምብሬን አቋም ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል። ለወንዶች 550 ሚ.ግ. ለሴቶች 425 ሚ.ግ. ክሎሪን በቀን ያስፈልጋል።አስር እግር ያለው ባለቅርፊት አሳ 36% የቀን ክሎሪን ፍላጐታችንን ያቀርባል። ✔ክሮሚየም! ክሮሚየም ፋትን፣ ፕሮቲን፣ እና ካርቦሃይድሬት ለመፍጨት ያገለግላል። 35 ማይክሮግራም በቀን ያስፈልገናል ሴቶች 25 ማይክሮ ግራም ያስፈልጋቸዋል። ግማሽ ኩባያ ብርኮሊ 11 ማይክሮ ግራም ክሮሚየም ይሰጠናል። ✔ኮፐር! ኮፐር አጥንት እና የተለያየ የሰውነት ክፍላችን ተቀናጅተው እንዲሰሩ ያደርጋቸዋል በተጨማሪም ሀይል/ጉልበት ይሰጣቸዋል። 700 በቀን ለወንድ እና ሴት ያስፈልጋቸዋል። ✔ፍሎራይድ! ፍሎራይድ ጥርስ እንዳይጐዳ ይከላከላል ጤናማ የሆነ አጥንት ለመገንባት ይጠቅማል። ከ0.1-0.5 ሚ.ግ. ለህፃናት፣ 4 ሚ.ግ. ለአዋቂ ወንድ 3 ሚ.ግ. ለአዋቂ ሴቶች በቀን ያስፈልጋቸዋል። አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ከመጠጥ ውሃ የፍሎራይድ ፍላጐታችንን እናሟላለን። ✔ፎሌት! ፎሌት የደም ሴሎቻችን እንዲመረቱ ለማድረግ ይጠቅማል በተለይ ለእርጉዝ ሴቶች ይጠቅማል። 300 ዮጂኤስ ለሴቶችን ወንዶች በቀን ያስፈልጋል። አንድ ኩባያ ምስር 90% የፎሌት ፍላጐታችንን ያሟላል። ✔አዮዲን! አዮዲን ጤናማ የታይሮይድ ሆርሞን እንዲመረት ያደርጋል። 95 ዮጂኤስ በቀን ለወንድ እና ሴቶች ያስፈልጋል። ስካሎፕ 90% የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል። ✔ብረት(IRON)! ብረት (Iron) ኦክስጂን ወደተለያየ የሰውነት ክፍል ወስጥ እንዲሰራጭ ያደርጋል በተጨማሪም ሀይል/ጉልበት እንዲመረት ድጋፍ ያደርጋል። 6 ሚ.ግ. ለወንድ 8.1 ሚ.ግ. ለሴቶች በቀን ያስፈልጋል። አንድ ኩባያ ስፒናች (አረንጓዴ የሚበላ ቅጠል) 36% የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል። ✔ማንጋኒዝ! ማንጋኒዝ ለቆዳ ጤንነት፣ ጐጂ አንቲኦክሲዳንት በመከላከል፣ ጤናማ የስኳር መጠን እንዲኖረን በማድረግ ይጠቅመናል። 2-5 ሚ.ግ. በቀን ለአዋቂዎች ያስፈልጋቸዋል። አንድ ኩባያ ቡናማ ሩዝ 88% የማንጋኒዝ ፍላጐታችንን ያሟላል። ✔ማግኒዚየም! ማግኒዚየም ሰውነታችን ጉልበት/ሀይል እንዲያመነጭ ያደርጋል፣ የነርቭ ስርዓታችንን ያመጣጥናል፣ የሰውነት መቆጣትን ይቆጣጠራል፣ የደም ስኳር መጠንን ይቆጣጠራል። 350 ሚ.ግ. ለወንዶች 265 ሚ.ግ. ለሴቶች በቀን ያስፈልጋል። ሩብ ኩባያ የድባ ፍሬ 48% የማግኒዚየም የቀን ፍላጐታችንን ያሟላል። ✔ኒያሲን! ኒያሲን ጉልበት/ሀይል ለማምረት ጠቃሚ ነው ጐጂ አንቲኦክሲዳንቶችን በመከላከል በሽታ እንዳይከሰት ያደርጋል። 12 ሚ.ግ. ለወንድ 11 ሚ.ግ. ለሴቶች በቀን ያስፈልጋል። የዶሮ ስጋ 97% የቀን ፍጆታችንን ያበረክታል። መልካም ጤንነት!!!
0 Comments 0 Shares