አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2009 (2009) የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዘመናዊ የአውሮፕላን ማቆሚያ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ አዋለ።
በአውሮፕላን ማረፊያው ተግባራዊ የተደረገው “Advanced Visual Docking Guidance System (A-VDGS)” የተባለው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጀበ የአውሮፕላን ማቆሚያ መሣሪያ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ ጠቅሷል።
ቀልጣፋ፣ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ሆኖ ሥራ ላይ የዋለው ይህ መሣሪያ ከ778 ሺህ ዩሮ በላይ ወጪ ተደርጎበታል ነው ያለው።
አገልግሎቱ በሰው ሃይል ሲሰጥ በነበረበት ጊዜ አንድን አውሮፕላን የማቆም ስራ ማኮብኮቢያ ላይ ካረፈ በኋላ እስከ ማቆሚያው ድረስ ከአውሮፕላን አብራሪው ጋር በመነጋገር የሚከናወን ስለነበር ችግሮች እንደነበሩበት ድርጅቱ ጠቅሷል።
በባለሙያዎች የመረጃ ልውውጥ ሂደት አለመግባባት መኖር፣ አውሮፕላኖችን ያለቦታቸው ማቆም፣ የመንገደኞች መሸጋገሪያ ድልድይ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመገኘትና በአውሮፕላን ማቆሚያው መኖር የሌለባቸው አካላት መገኘት ከችግሮቹ መካከል ተጠቃሽ መሆናቸው ተነግሯል።
በመሆኑም በአውሮፕላን ማረፊያዎች አደጋ እንዳያጋጥም አስቀድሞ ለመከላከል ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት በመስጠት ላይ ከሚገኙ 52 የአውሮፕላን ማቆሚያዎች በ14ቱ ላይ የመሣሪያዎች ተከላና ሙሉ በሙሉ በመረጃ መረብ የማገናኘት ሥራ መከናወኑ ተነግሯል።
ቴክኖሎጂው በሰዎች ይፈጠር የነበረውን ስህተት ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ሲሆን ከአንድ ማዕከላዊ ቦታ ላይ በዲጂታል ሥርዓት አስራ አራቱንም ማቆሚያዎች መቆጣጠር እንደሚያስችልና ጊዜን እንደሚቆጥብ ድርጅቱ ጠቅሷል።
ቴክኖሎጂው የአውሮፕላኑን ዓይነት፣ ርቀትና አቅጣጫን ከጊዜ ጋር በማጣመር ለአብራሪዎች ተመሳሳይና ትክክለኛ መረጃን በመስጠት አውሮፕላኑ የሚቆምበትን ቦታ በማሳወቅ ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል።

0 Comments
0 Shares