ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከሳዑዲ አረቢያ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

መቀሌ ግንቦት 21/2009 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ህገ ወጥ ስደተኞች ከአገሪቱ እንዲወጡ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች ወደአገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ጥሪ አቀረበ።

የማህበሩ የቦርድ አባል መምህር ያሲን ራጀኡ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ስደተኞቹ ወደ አገራቸው በክብር እንዲመለሱ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያስተላለፈውን ውሳኔና የጊዜ ገደብ ማክበር አለባቸው።

እንደ መምህር ያሲን ገለጻ፣ የሳዑዲ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገሩ የገቡ ስደተኞች ከአገሪቱ እንዲወጡ መልዕክት ያስተላለፈው ለአገርቱ ደህንነት ሲባል መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያውያኑ ጊዜው ሳያልፍ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው።

የተላለፈውን አዋጅ ተከትለው ወደአገራቸው መመለስ የጀመሩ ህገ ወጥ ስደተኞች ቢኖሩም አንዳንዶቹ ሰምተው እንዳልሰሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

" የሳዑዲ መንግስት ያስተላለፈው ውሳኔ የተለመደ ነው፣ ግማሹን ካስወጣ በኋላ ለእኛ ምህረት ያደርግልና " በሚል እስካሁን ያልወጡ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን መምህር ያሲን ጠቁመዋል።

ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳያልፍ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ወላጆችም ልጆቻቸው በሰላም ወደአገራቸው እንዲመለሱ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ መምህር ያሲን አስገንዝበዋል።

"በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች በገጠር አካባቢ ይገኛሉ" ያሉት መምህር ያሲን፣ አሁን አዋጁን አክብረው ከአገሪቱ ካልመጡ የከፋ ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል አመልክተዋል።

መምህር ያሲን እንዳሉት የሳዑዲ መንግስት ከአገርቱ አንወጣም ያሉ ህገወጥ ስደተኞችን ለማሰር ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች 98 እስር ቤቶችን አዘጋጅቷዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ በሰላም እንዲመለሱ በሪያድና በጅዳ 18 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቶ ጊዜያዊ ፓስፖርት አዛጋጅቶ እየጠበቃቸው በመሆኑ እድሉን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር አባላት በቅርቡ ወደሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ዜጎች ያለችግር በሰላም ወደአገራቸው እንዲመለሱ የመቀስቀስና የማስገንዘብ ሥራ እንደሚሰሩ አስረድተዋል።

በሳዑዲ አረቢያ ለስድስት ዓመት መቆየቷዋን የተናገረችው የአድዋ ከተማ ነዋሪ ወጣት ክብራ ገብረማሪያም፣ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ የሚደርስባቸው እንግልት ከባድ መሆኑን ተናግራለች።

በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን " ወደ አገሬ ተመልሼ ምን እሰራለሁ " በሚል የተሳሰተ አመለካከት ራሳቸውን ለተለያዩ ችግሮች ማጋለጥ እንደሌለባቸው መክራለች።

ከሳዑዲ አረቢያ ወደአገሯ ከተመለሰች አንድ ወር እንደሆናት የተናገረችው ወጣት ክብራ፣ "ወጣቶች በአገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ አምነው በሰላም መመለስ አለባቸው" ብላለች።

" በአገር ሰርቶ መጠቀም ክብር ነው፤ ሳዑዲ አረቢያ ሂደን ውርደት እንጂ ክብር አላገኘንም " ያሉት ደግሞ ሦስት ጊዜ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የመጡት አቶ ናይዝጊ ዝግታ የተባሉ የአድዋ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች ምንም ሀብት ሳናፈራና ከአገር ለመውጣት የተበደርነውን ገንዘብ ሳንከፍል እንዴት እንመለሳለን የሚል አስተሳሰብን ወደጎን በመተው ወደአገራቸው መመለስ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትግራይ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎይቶኦም ይብራህ በበኩላቸው፣ በ2009 ዓ.ም በትግራይ ክልል ሥራ አጥ ወጣቶች ተብለው የተለዩ 401 ሺህ ወጣቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከል በሥራ ላይ ለመሰማራት የተመዘገቡት 90 በመቶ የሚሆኑን ብቻ መሆናቸውን ገልጸው በህገ ወጥ ተሰደው የሄዱ የክልሉ ወጣቶች ወደአገራቸው ሲመለሱ በእዚህ እንዲታቀፉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።

Source: http://www.ena.gov.et/index.php/social/item/14734-2017-05-29-15-55-08
ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ከሳዑዲ አረቢያ እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ መቀሌ ግንቦት 21/2009 የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ህገ ወጥ ስደተኞች ከአገሪቱ እንዲወጡ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች ወደአገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር ጥሪ አቀረበ። የማህበሩ የቦርድ አባል መምህር ያሲን ራጀኡ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ስደተኞቹ ወደ አገራቸው በክብር እንዲመለሱ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ያስተላለፈውን ውሳኔና የጊዜ ገደብ ማክበር አለባቸው። እንደ መምህር ያሲን ገለጻ፣ የሳዑዲ መንግስት በህገ ወጥ መንገድ ወደ አገሩ የገቡ ስደተኞች ከአገሪቱ እንዲወጡ መልዕክት ያስተላለፈው ለአገርቱ ደህንነት ሲባል መሆኑን በመገንዘብ ኢትዮጵያውያኑ ጊዜው ሳያልፍ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው። የተላለፈውን አዋጅ ተከትለው ወደአገራቸው መመለስ የጀመሩ ህገ ወጥ ስደተኞች ቢኖሩም አንዳንዶቹ ሰምተው እንዳልሰሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። " የሳዑዲ መንግስት ያስተላለፈው ውሳኔ የተለመደ ነው፣ ግማሹን ካስወጣ በኋላ ለእኛ ምህረት ያደርግልና " በሚል እስካሁን ያልወጡ በርካታ ዜጎች መኖራቸውን መምህር ያሲን ጠቁመዋል። ይህ የተሳሳተ አስተሳሰብ በእጅጉ የሚጎዳ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳያልፍ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። ወላጆችም ልጆቻቸው በሰላም ወደአገራቸው እንዲመለሱ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ መምህር ያሲን አስገንዝበዋል። "በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች በገጠር አካባቢ ይገኛሉ" ያሉት መምህር ያሲን፣ አሁን አዋጁን አክብረው ከአገሪቱ ካልመጡ የከፋ ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል አመልክተዋል። መምህር ያሲን እንዳሉት የሳዑዲ መንግስት ከአገርቱ አንወጣም ያሉ ህገወጥ ስደተኞችን ለማሰር ከፍተኛ ሙቀት ባለባቸው አካባቢዎች 98 እስር ቤቶችን አዘጋጅቷዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹ በሰላም እንዲመለሱ በሪያድና በጅዳ 18 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችን ከፍቶ ጊዜያዊ ፓስፖርት አዛጋጅቶ እየጠበቃቸው በመሆኑ እድሉን በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ማህበር አባላት በቅርቡ ወደሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ዜጎች ያለችግር በሰላም ወደአገራቸው እንዲመለሱ የመቀስቀስና የማስገንዘብ ሥራ እንደሚሰሩ አስረድተዋል። በሳዑዲ አረቢያ ለስድስት ዓመት መቆየቷዋን የተናገረችው የአድዋ ከተማ ነዋሪ ወጣት ክብራ ገብረማሪያም፣ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሳዑዲ አረቢያ የሚደርስባቸው እንግልት ከባድ መሆኑን ተናግራለች። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን " ወደ አገሬ ተመልሼ ምን እሰራለሁ " በሚል የተሳሰተ አመለካከት ራሳቸውን ለተለያዩ ችግሮች ማጋለጥ እንደሌለባቸው መክራለች። ከሳዑዲ አረቢያ ወደአገሯ ከተመለሰች አንድ ወር እንደሆናት የተናገረችው ወጣት ክብራ፣ "ወጣቶች በአገራቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ አምነው በሰላም መመለስ አለባቸው" ብላለች። " በአገር ሰርቶ መጠቀም ክብር ነው፤ ሳዑዲ አረቢያ ሂደን ውርደት እንጂ ክብር አላገኘንም " ያሉት ደግሞ ሦስት ጊዜ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የመጡት አቶ ናይዝጊ ዝግታ የተባሉ የአድዋ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ኢትዮጵያውያን ህገ ወጥ ስደተኞች ምንም ሀብት ሳናፈራና ከአገር ለመውጣት የተበደርነውን ገንዘብ ሳንከፍል እንዴት እንመለሳለን የሚል አስተሳሰብን ወደጎን በመተው ወደአገራቸው መመለስ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የትግራይ ክልል ስፖርትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎይቶኦም ይብራህ በበኩላቸው፣ በ2009 ዓ.ም በትግራይ ክልል ሥራ አጥ ወጣቶች ተብለው የተለዩ 401 ሺህ ወጣቶች መኖራቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ መካከል በሥራ ላይ ለመሰማራት የተመዘገቡት 90 በመቶ የሚሆኑን ብቻ መሆናቸውን ገልጸው በህገ ወጥ ተሰደው የሄዱ የክልሉ ወጣቶች ወደአገራቸው ሲመለሱ በእዚህ እንዲታቀፉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል። Source: http://www.ena.gov.et/index.php/social/item/14734-2017-05-29-15-55-08
0 Comments 0 Shares